ኢትዮጵያን ከገጠሟት ፈተናዎች አውጥቶ ወደ ብልፅግና ለማሻገር በሚደረገው ጥረት የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎና የምርጫ ሚና ወሳኝ ነው፦ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ

Spread the love

​የብልፅግና መንግስት በለውጥ ሂደቱ የገጠሙትን ዘርፈ ብዙ ፈተናዎች ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር ለተመዘገቡ ድሎች የሴቶች ክንፍ አደረጃጀቶች መላውን ሴት በማስተባበር የላቀ ሚና መጫወታቸውን የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ስራ አስፈፃሚና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ ገለጹ።

​በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ጽህፈት ቤት አስተባባሪነት “በሴቶች ተሳትፎ የፀናችና የበለፀገች ኢትዮጵያ!” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ የምክክር መድረክ በሚዛን አማን ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

​መድረኩን በንግግር የከፈቱት ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ እንደተናገሩት ሀገራዊ የብልፅግና ግቦችን ለማሳካት በሚደረገው ርብርብ ውስጥ ሴቶች በፖለቲካው መስክ ያላቸው ተሳትፎና በምርጫ ሂደት የሚኖራቸው ንቁ ተሳትፎ የፀናች ሀገር ለመገንባት መሰረት መሆኑን ጠቁመዋል።

መንግስት በለውጥ ጉዞው የገጠሙትን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ፈተናዎች በማለፍ ላስመዘገባቸው ውጤቶች ሴቶች በየደረጃው የነበራቸው የማስተባበር አቅም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ነበረው።

​የተዛባ የፖለቲካ ባህልን በማረም እና ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር እንዲኖር ለማድረግ የሴቶች በምርጫ መሳተፍና በፖለቲካ ውሳኔ ሰጪነት መጎልበት አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን አሳስበዋል።

​የሴቶችን የኢኮኖሚ ማነቆ ለመፍታት በተቀረጹ ፖሊሲዎችና በ”ሌማት ቱሩፋት” መሰል የልማት ኢኒሼቲቮች ሴቶች እያሳዩት ያለው ውጤታማነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

​በመድረኩ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የደቡብ ምዕራብ ሴቶች ክንፍ አስተባባሪ እና የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ህይወት አሰግድ በበኩላቸው ብልፅግና ፓርቲ ሀገርን ከመበተን የታደገ እና በውሳኔ ሰጪነት ቦታዎች ላይ ለሴቶች 50 በመቶና ከዚያ በላይ ድርሻ በመስጠት በተግባር የሴቶችን ተጠቃሚነት ያረጋገጠ ፓርቲ መሆኑን ገልጸዋል።

በመድረኩ ላይ የክልሉና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ከተለያዩ መዋቅሮች የተውጣጡ ሴቶች እየተሳተፉ ሲሆን በወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *