
በክህሎት ልማት እና በስራ ዕድል ፈጠራ ውጤታማ ስራዎችን ማከናወን ተችሏል
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ የተጣለበትን ስትራቴጂያዊ ግቦችን ከማሳካት አንፃር ውጤታማ ስራዎችን ማከናወኑን አስታዉቋል፡፡
በህብረተሰቡ ውስጥ ዘመናዊ የመረጃ ቴክኖሎጂን በመዘርጋትና በማስፋፋት ለህብረተሰቡ አስፈላጊ መረጃዎችን እንዲያገኙ በማድረግ በክህሎት ልማት፣በስራ ዕድል ፈጠራ፣በሰላማዊ የኢንዱስትሪ ግኑኝነት እና በሙያቸዉ የበቁ ዘጎችን ከማፍራት አንፃር ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰራ እንደሚገኝም ተቁሟል፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዐቢይ አንደሞ እንዳሉት፤ቢሮዉ የተጣለበትን ስትራቴጂያዊ ግቦችን ከማሳካት አንፃር እስካሁን ባለዉ አፈጻጸም ውጤታማ ስራዎች ተከናዉኗል፡፡
ተቋማዊ አቅምና ብቃት ለማሳደግ የ683 ኮሌጅ አሰልጣኞችን የአቅም ግንባታ ስልጠና ለመስጠት ታቅዶ ይህም ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን በማሰልጠኛ ተቋማት ተበላሽተው አገልግሎት የማይሰጡ 26 ማሸኖችን ጠግኖ ወደ ስራ ለማስገባት መቻሉን ገልጸዋል፡፡
እንደ ዶክተር ዐቢይ አንደሞ ገለጻ፤አራት የተጠናከረ የሥልጠና ተቋማት የክላስተር አደረጃጀት እንድኖር እና በቁጥር 20 ተቋማት የቦርድ አስተዳደር ስርዓትን እንድተገብሩ መደረጉንና የመንግስት ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት የዉስጥ ኦዲት ለማድረግ መቻሉን ተናግረዋል፡፡
በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት ከውስጥ ገቢ 6ሚሊዬን 9መቶሺህ ብር የተሰበሰበ ሲሆን በኮሌጆች 12 ኢንተርፕራይዞችንም ለማቋቋም ተችሏል፡፡ እነዚህም፡-በቴፒ ፖሊ ቴክኒክ 3፣በማሻ ኮንስትራክሽንን ኢንዳስትሪያል ኮሌጅ 2፣ በቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 3፣ በአማን ፖሊ ቴክኒክ 3፣እንዲሁም በኢሰራ ባሌ ኮንስትራክሽንና ኢንዳስትሪል ኮሌጅ 1 ኢንተርፕራይዞችን ለማቋቋም እንደተቻለም አስረድተዋል፡፡
በሁሉም አሬንጓዴ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ለመፍጠር ትኩረት በመስጠት ከ1/11/2017 ዓ/ም ጀምሮ ተቋማት ማራኪ ምቹና ለማህበረተሰብ የዕውቀትና የሀብት ማፍሪያ ቦታ እንድሆኑ ሁሉም ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ለምግብነትና ለጥላ የሚውሉ ዛፎችን የመትከል፣የመንከባከብ እና የኦዲት ሥራዎች በብዛትና በጥራት መሰራቱን የጠቀሱት ዶር ዓቢይ አንደሞ ለሁለቱም አገለግሎት የሚዉሉ(ለምግብነትና ለጥላ) የሚውል ችግኝ ተከላ ስራ(ማንጎ፣ፓፓያ፣ካሳባ፣እንሰት፣ቡና፣አባካዶ፣ሙዝ)በአራቱም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች እና በ16 ኮንስትራክሽና ኢንዳስትሪያል ኮሌጆች ዉስጥ ከ54 ሺህ7መቶ በላይ ችግኞችን መትከል መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡
ኮሌጆች የኢንተርፕራዝ መፈለፈያ ማዕከል ማድረግ አንዱ የዘርመሎ እሳቤ ስሆን በያዝነዉ በጀት ዓመት በ6 ወራት 12 ኢንተርፕራዞችን በማደራጀት ውጤት መመዝገቡን ጠቁመዋል፡፡
አድሱ እሳቤ ስልጠና ከወረቀት በላይ እና ከዳቦ በላይ ኢንቴርፕሪነር የመሆን ዕድል የሰጠበት እና በፋብርፕኬሽን ዘርፍ ከ3.7 ሚሊዮን ብር በላይ የማግኘት ዕድል መፍጠሩን ነዉ ዶክተር ዓቢይ የገለጹት፡፡
በተጨማሪም የንቅናቄ ሥራዎች፣የገጽታ ግንባታ፣መሰረተ ልማት የማሟላትና ወርክ ሾፖችን የማደራጀትና ማስዋብ ሥራዎች በሁሉም ደረጃ የተሰራ ቢሆንም የማህበራዊ ሚድያ አንቅዎችን፣ የምሁራን ማህበርና ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎችና ወጣቶች ጋር በቅንጅት ሥራዎችን የመሥራትና ምድረ ግቢ የማስዋብ ሥራዎች በተደራጀ መልኩ የመሥራትና ኅብረተሰቡን የማስተዋወቅ ሥራዎችን ከባለፈዉ ዓመት በተሻለ መልኩ ለመስራት መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡ ለአብነትም፡- ቴፒ ፖሊ ቴክኒክ(ቴፒ ከተማ ወጣቶች ግብ የማስዋብ፣ የከተማ ስፖርት ቡድን ማሊያ ላይ የኮሌጁን ዓርማና ሎጎ የማሳተም፣የአከባቢ ማህብረተሰብ በችግኝ ተከላ በንቃት የመሳተፍ (አንድራቻ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ፣ቦንጋ ፖሊ፣አማን ፖሊ) ይጠቀሳሉ፡፡
በተለይ፤የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ጥራትና አግባብነት ለማሳደግ በትብብር ስልጠና፣በሙያ ጋይዳንስና ካውንስሊንግ እና በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰልጣኞችን በማሳተፍ መተግበር ተችሏል፡፡
በፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች የዞኒንግ ልየታ ጥናትን መሰረት በማድረግ መውጫ (Exit) ስትራቴጅ ማዘጋጀት፣የስልጠና ማቴሪያል ማሟላትና አዲስ የወርክሾፕ ለውጥ እንድያደርጉ ለማድረግ ታቅዶ መውጫ (Exit) ስትራቴጅ ማዘጋጀትና የስልጠና ማቴሪያል ማሟላት መቻሉን አዉስተዉ አዲስ ወርክ ሾፒ የማደራጀት ስራ ገና ብዙ ሀብት የሚጠይቅ እንደሆነ መገምገሙንም አስረድተዋል፡፡
ለዘጎች በቋሚና በጊዜያዊ የሥራ ዕድል ከመፍጠር አንፃር24ሺህ 210 በቋሚ እና ለ28ሺህ 253 ዜጎች ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፈጠሩን እና ለዜጎች ከተፈጠረው የስራ ዕድል ፈጠራ አኳያም በግብርና 14ሺህ 8መቶ 45፣በኢንዱስትሪ 3ሺህ 6መቶ31 እና በአገልግሎት 5ሺህ 7መቶ 34 ድርሻ መያዙን ያብራሩት ዶክተር አብይ አንደሞ በቋሚ ስራ ዕድል ፈጠራ ውስጥ 2151 በአደረጃጀት የተፈጠረ ስራ ስሆን በኢንተርፕራይዝ 19ሺህ131 ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አክለዋል፡፡
ለሥራ ዕድል ፈጠራ በየደረጃዉ ካሉ መዋቅሮች 85ሚሊዬን 520ሺህ በላይ) ሀብት ለማስመሰብ የተቻለ ስሆን ከዚህም ወደ ኦሞ የተላለፈዉ 30 ሚሊዬን 1መቶ ሺህ ብር መሆኑንና የገበያ ድጋፍና ትስሰር መደረጉን አስረድተዉ የኢንተርፕራይዞች ዕድገት ደረጃ ማሸጋገርና ምርጥ ተሞክሮ ለመቀመርኢንተርፕራይዞችን በተለያዩ ዕድገት ደረጃ እንዲሸጋገሩ ለማድረግ በተደረገዉ ጥረት 40 አዲስ ሞዴል ኢንተርፕራይዞችን ለመለየት መቻሉን አብራርተዋል፡፡
አያይዘዉም፤ለአዲስ የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀሲንዎች ህጉ ባስቀመጠው መስፈርት መሠረት ፈቃድ ለመስጠት ታቅዶ ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን የዉጭ ሥራ ስምሪት አገልግሎት ለማስፋፋትመስፈርቱን አሟልተው ወደ ውጭ ሀገር ሄደው ለመስራት የሚፈልጉ ዜጎችን መረጃ ማደራጀትና ወደ ዉጪ ሀገር ለሥራ እንድሰማሩ ለማድረግ 2ሺህ 9መቶ39 ታቅዶ 1ሺህ500 መተግበሩን ጠቁመዋል፡፡
በመጨረሻም በ2018 ዓ.ም በግልና በመንግስት ኮሌጆች የተያዘ ምዘና ፕሮግራም መሰረት ለመስጠት ታቅዶ በሁሉም የመንግሰት ኮሌጆችና የግል ኮሌጆች በተያዘው ጊዜ ሠሌዳ መሰረት ምዘናው መሰጠቱን በመግለጽ ተመዝነዉ ብቁ ለሆኑ ተመዛኞች ሰርተፊኬት በመስራት መሰራጨቱን እንዲሁም በLMIS መረጃ ከኮሌጆች የተላከ የተመዛኞች መረጃ ወደ ዳታቤዝ ሲስተሙ እንዲገባ መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡
በምዘና መሳሪያ ዝግጅትና አያያዝ ተገቢውን ቁጥጥርና ክትትል ማድረግ የምዘና መሳሪያ ሁለንተናው ጥንቃቄ እንዲደረግና ምስጥራዊነቱ የጠበቀ እንዲሆንና የተዘጋጁትን የምዘና መሳሪያዎችን በሙያ ዓይነትና በደረጃ በመለየት የማደራጀት ሥራ መከናወኑን ዶክተር አብይ ገልጸዋል፡፡
በካሳሁን አሰፋ
