ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ ላይ ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፡-

Spread the love

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ ላይ ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፡-

•በአማራ እና ኦሮሚያ ክልል ግጭትን በሚመለከት በየሰፈሩ በአማራም በኦሮሚያ ውስጥም ግጭቶች ይታያሉ፤ እነዚህ ግጭቶች ሰው የሚገሉ ንብረት የሚያወድሙ እንዲሁም ከጉዟችንን የሚያዘገዩ አላስፈላጊ ነገሮች ናቸው፤
•የእኛ መሻት ሁልጊዜም ሰላም ነው፤ የምንናገረው የምንተጋው፣ አብዝተን የምንሻው ሰላም በሀገራችን እንዲሰፍን ነው፣

•ኢትዮጵያን ሳታንስብንና ሳንቦጫጭቃት ብንጠግናት ብንሰራላት ብናበለጽጋት ግን ሀገራችን እንደ ስመጥር ሀገራት መሆን የሚያስችል ብቃት አላት፣

•ህዝብን ከሚያውክ ሀገርን ከሚያዳክም እርስ በእርስ ከሚያገዳድል ነገር መጠበቅ ያስፈልጋል፣

•አማራ እና ኦሮሞ በተደጋጋሚ እንዳነሳሁት ቢፈልጉም ባይፈልጉም በሰላም ለመኖር ያላቸው ምርጫ አንድ ብቻ ነው፤ ያንድ አባት ልጆችና የአንድ ሀገር ዜጎች እንዲሁም ወንድማማች መሆናቸውን አውቀው በተከባበረ አብሮ መኖር በሚያስችል ማንነት መጓዝ ብቻ ነው፣

•ታሪክ ሙያዊ ዘርፍ ነው፣ ሁሉም ሰው ታሪክን እኩል አይረዳውም፤ እኩል አይናገረውም፤ እኩል አይጽፈውም፤ በዘርፉ የተማሩ እንዴት ታሪክ እንደሚመረመር የሚያውቁ ሰዎች አሉ፣ሰዎች አሉ፡፡

•በአማራና በትግራይ ክልል መካከል ጥያቄ የሚነሳባቸው ቦታዎችን በሚመለከት ህግን የተከተለ፣ ዘላቂ ሰላምን ያከበረና የህዝብን አብሮነት ያስቀደመ የመፍትሄ አቅጣጫ እንከተል ብለን እየሰራን ነው፡፡

•ነገር ግን የእኛ ብቻ መፍትሄ ይተግበር አላልንም፡፡ ለዘላቂ ሰላምና ህዝቦች አብሮነት የሚሆን መፍትሄ ለሚያመጡ አካላትም በራችን ክፍት ነው፡፡

•የእኛ ፍላጎት በሁለቱም ክልሎች መካከል ዘላቂ ሰላም ሰፍኖ ማየት ነው፡፡ የህዝቡም ፍላጎት ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *