በጎነትን ለማስረጽ እና የአብሮነት እሴቶችን ለማጎልበት የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ሚና ከፍተኛ ነው ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት መኩሪያ ገለፁ።

Spread the love

የ2016 የወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልገሎት ተሳታፊዎች በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን የተለያዩ በጎ ተግባራትን አከናውነዋል ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት መኩሪያ እንደገለፁት ወሰን ተሻጋሪ የክረምት ወራት በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ሠላምን አስተማማኝና ዘላቂ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ውጤታማ ለማድረግ ሚናቸው የጎላ ነው ብለዋል።

ጠንካራ ሀገረ መንግስት በመገንባት ኢትዮጵያን ወደ ቀደመ ከፍታዋ በመመለስ እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን ይበልጥ ስኬታማ ለማድረግ የወጣቶችን ተሳትፎ ማስፋፋት ወሳኝ መሆኑንም ኃላፊዋ አስረድተዋል።

ወጣቶቹ የሀገራቸው ጠቃሚ ዕሴቶችን የሚያሳድጉበት፣ የህይወት ክህሎትን፣ ልምድና ባህሎችን የሚቀስሙበት ይሄው ሂደት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ቢሮው ከለድርሻዎች ጋር ቅንጅታዊ አሰራሩን አጠናክሮ ይቀጠላል ብለዋል።

ጉዳዮ የሚመለከታቸው ሁሉ ለተግባሩ ቀጣይነትና ስኬታማነት ኃላፊነታቸውን በተገቢው እንዲወጡ ወ/ሮ ገነት ጠይቀዋል።

የታርጫ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዳዊት ወንድሙ በበኩላቸው የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ሰዎች ጊዚያቸውን፣ ገንዘባቸውን፣ ጉልበታቸውንና እውቀታቸውንና አምነው የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ነው ብለዋል።

እንደ ታርጫ ከተማ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ ሥራዎች በመሰራት ላይ ይገኛል ያሉት ካንቲባው ተግባሩን አጠናክሮ ለማስቀጠል አስተዳደሩ ያላሰለሰ ጥረት እያደሰገ ነው ብለዋል።

የዳውሮ ዞን ሴቶች፣ ህጻናት ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ብርሃኔ ብሩ ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በጎነትን ለማስረጽ እና አብሮነትን ለማጠናከር እያበረከቱተት የሚገኘው የዜግነትን ኃላፊነት የሚደነቅ ነው ብለዋል።

በጎ አድራጊዎች ለሚኖሩበት ማህበረሰብ፣ ልማትና ለአካባቢ ደህንነት እያበሰከቱ ያለው አስተዋጽኦ ዘላቂ እንዲሆን ሁሉም ልተባበር እንደሚገባም ኃላፊዋ አስገንዝበዋል።

የዘንድሮ ወሰን ተሻጋሪ የክረምት ወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት “በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ!” በሚል መሪ ሀሳብ ለ3ኛ ጊዜ ከ13ቱ የስምሪት መስኮች መካከል የችግኝ ተከላ፣ ደም ልገሳ፣ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ላይ ግንዛቤ የመፍጠርና አካባቢ ጽዳት ሥራ በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ተከናውኗል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *