
በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት አዘጋጅነት ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖሊቲካ ፓርቲዎች ያደረጉት ጥልቅና ጠንካራ የክርክር መድረክ በዚህኛው ዙር በኢኮኖሚ ዘርፍ ላይ ያተኮረ ነው።
ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎቹም ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በአማራጭ የፖሊሲ የክርክር መድረክ “በፍትሐዊ የኢኮኖሚ ሥርዓት ግንባታና የዜጎች ተጠቃሚነት” ላይ ጠንካራ ክርክር አድርገዋል። የሰለጠነና ጥልቅ ሙግት በተደረገበት በዚህ እጅግ አጓጊ የክርክር መድረክ ፦
የብልፅግና ፓርቲ
ኢሶዴፓ
ሠላም ለኢትዮጵያ ጥምረት
ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ
በኢኮኖሚ ፖሊሲ ላይ የሚከተሉትን ርዕዮተ ዓለምና አማራጭ ሃሳባቸውን ይዘው ቀርበዋል፤ ተሟግተዋል፡፡ በሰለጠነና ዴሞክራሲያዊ መንገድም ብርቱ ክርክር አድርገዋል።
ይህን ብርቱ ሙግት አርብ ምሽት 2፡40 ጀምሮ በደቡብ ቴሌቪዥንና በዲጅታል ሚዲያ አማራጮች እንዲሁም በደቡብ ድምፅ ሬዲዮ ኤፍ ኤም 100.9 ይከታተሉ፡፡
በድጋሚ ቅዳሜ ከቀኑ 7:40 እስከ 9:40 እንዲሁም ምሽት 2:40 በማኅበራዊ ሚዲያዎቻችን እና በደቡብ ቴሌቪዥን ይጠብቁን!!
