በኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽንና በደቡብ ምዕራብ ማዕድን ኮርፖሬሽን መካከል የጋራ ልማት ስምምነት ተፈረመ

Spread the love

በኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን መካከል በደቡብ ምዕራብ ክልል የሚገኘውን የማዕድን ሀብት በጋራ ለማልማት የሚያስችል የውል ስምምነት እና የመግባቢያ ሰነድ ተፈርሟል።

የስምምነቱ ውል በክልሉ የሚገኙ የማዕድን ሀብቶችን በዘመናዊ መንገድ አልምቶ ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገትና ለሥራ ዕድል ፈጠራ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ዓላማ ያደረገ ነው።

በውሉ መሠረት የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን ለልማቱ አስፈላጊ የሆነውን ካፒታል፣ ማሽነሪና የቴክኒክ ባለሙያዎችን የማሰማራት ኃላፊነት የሚወጣ ሲሆን የደቡብ ምዕራብ ማዕድን ኮርፖሬሽን ደግሞ የማምረቻ ይዞታዎችን ለሥራ ዝግጁ የማድረግና የአካባቢውን ሰላም የማስከበር ኃላፊነቱን እንደሚወጣም ተገልጿል።

በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ ቤት ኃላፊና የክልሉ ማዕድን ኮርፖሬሽን ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ፍቅሬ አማን እንደገለፁት ሁለቱም ተቋማት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች በመሆናቸው በመካከላቸው ያለውን አጋርነት በማጠናከር፣ በመተጋገዝ እና በመተባበር የታቀዱ የልማት ሥራዎችን በፍጥነትና በጥራት ወደ ሥራ እንዲያስገቡ አሳስበዋል።

በመድረኩ ላይ የቦርድ አመራሮች፣ የሁለቱም ኮርፖሬሽኖች ሥራ አስፈጻሚዎች እና ከፍተኛ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *