በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሱፐርቪዥን ቡድን በሼይ ቤንች ወረዳ ሲዝ ከተማ የድጋፍና ክትትል ስራዎችን እያካሄደ ነው

Spread the love

‎የክልሉ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊና የክልሉ ሱፐርቪዥን ቡድን አባል የማታለም ቸኮል (ኢ/ር) ፣ ሌሎች የዞን፣ የወረዳና የከተማ አስተዳድር አመራሮች በቤንች ሸኮ ዞን ሼይ ቤንች ወረዳ ሲዝ ከተማ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ምልከታ አድርገዋል።

በመስክ ምልከታው በሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቪ እየተሰሩ የእንስሳት እርባታ ማዕከል ሌሎች የልማት ስራዎችን ግብኝተዋል።

የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ የማታለም ቸኮል( ኢ/ር) መንግስት ለግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ የሰጠውን ትኩረትና የዘርፉን አዋጭነት በመረዳት እየተከናወነ ያለው አበረታች ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል።

መንግስት ለሰው ተኮር ለሆኑ የልማት ዘርፎች የሰጠውን ትኩረትና በአጭር ጊዜ ከድህነት ለመላቀቅ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያመላክት እንደሆነም ተገልጿል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *