በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ በሆኑት በአቶ ፍቅሬ አማን የተመራው የክልሉ የድጋፍ ቡድን በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ ተገኝተው የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች ግምገማ ማካሄድ ጀምሯል።

Spread the love

‎የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን በመግብያ እንደገለጹት የክልሉ አስተባባሪ አካላት በሁሉም ዞኖች ላይ በመከፋፈል የድጋፍ ስራ እያካሄደ መሆኑን ጠቅሰው ዓላማው ወቅቱ ትልቅ ትጋት የሚጠይቅ በመሆኑ ሀገራችንን ከሌሎች ሀገር ተርታ እንድትሰለፍ በፓርቲ የሚወርዱ ግቦችን ስኬታማ ለማድረግ ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል።

አክለውም በበጀት ዓመቱ በፓርቲ መሪነት የታቀዱ ተግባራት አፈፃፀማቸውን በመከታተል ጠንካራ ጎኖችን በማስፋትና ጉድለቶችን ለይቶ በማስተካከል በሁሉም አከባቢዎች የተግባር አንድነትን ለማምጣት ያደረገ በመሆኑ ሁሉም አመራር በስልጠና በተፈጠረው የሀሳብ አንድነትን ወደ ተግባር አንድነት ለመለወጥ በትጋት ተልዕኮዎችን መፈጸም አለባቸው ብለዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር የተቀመጡ የመቀነስ ግቦች፦ ኑሮ ውድነትን ለመቀነስ ምርትና ምርታማነትን ማረጋገጥ ፣ ሌብነትን መቀነስ ፣ ጠባቂነትን በመቀነስ ሁሉም በየደረጃው የድርሻውን መወጣት እንዳለበት ፣መንደርተኝነትን መቀነስ ፣የጭቃ ቤትን መቀነስ ፣ መሬትን ጻም ማሳደርን መቀነስ ያስፈልጋል ብለዋል አቶ ፍቅሬ።

በወረዳው በፓርቲ መሪነትና በንቅናቄ እየተሰሩ ያሉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች አፈጻጸም ሪፖርትን የጊምቦ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ታከገ መንገሻ በኩል እየቀረበ ይገኛል።

ቡድኑ በወረዳው በፓርቲና በፓርቲ ንቅናቄ እየተሰሩ ያሉ የልማት፣ የመልካም አስተዳደር ስራዎችን አፈፃፀም በመገምገም የተሰሩ ተግባራትን የተመረጡ ቀበሌዎች ላይ የመስክ ምልከታ እንደሚያደርጉ ተገልጿል።

‎በውይይቱ ላይ የካፋ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አጥናፉ ሀይሌ፣ የክልሉ ብልጽግና ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ዳንኤል ያዝን ጨምሮ የጊምቦ ወረዳ አስተባባሪ አካላት ተገኝተዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *