ባለፋት ዘጠኝ ወራት ወደ ውጭ ከተላከ የቡና ምርት ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

Spread the love

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ደበላ ያለፉት ዘጠኝ ወራት የቡና ንግድ አፈፃፀምን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ባለፋት ዘጠኝ ወራት ወደ ውጭ ከተላከ የቡና ምርት ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት 299 ሺህ 607 ቶን ቡና በመላክ ከእቅድ በላይ ማሳካት መቻሉንም ጠቅሰው፤ በዘርፉ የተገኘው የውጭ ምንዛሪም ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *