በክልሉ በስድስት ወራት ውጤታማ ተግባራት ተከናዉነዋል።ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር)

Spread the love

ምክርቤቱ በ2ኛው ውሎ በአስፈጻሚ ተቋማት በቀረበው የ6 ወራት አፈጻጸም ላይ በተነሱ አስተያየትና ጥያቄዎች ዙሪያ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ በክልሉ በኢኮኖሚው፣በማህበራዊ ልማት ስራዎች ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል፡፡

በክልሉ የልማት ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ በስፋት እየተሰራ እንደሚገኝም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል ፡፡

የልማት ስራዎችን ተደራሽ ለማድረግም መላው ህብረተሰቡን በማሳተፍ የልማት ፍላጎቶችን እያሳካን መሄዱን አጠናክረን እናስቀጥላለን ብለዋል፡፡

ያልተመለሱና ያልተፈቱ ህብረተሰቡ የሚያነሷቸው ጥያቄዎችን በመተባበር ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ከወትሮ በላቀ መንገድ እንሰራለን ሲሉም ተናግረዋል ፡፡

ባለፉት 6 ወራት በግብርናው ዘርፍ እያደገ የመጣ ለውጥ መኖሩን በምላሻቸው ተናግረዋል ፡፡

ለክልላዊና ሀገራዊ ኢኮኖሚ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ የተለያዩ ኢኒሼቲቮቭን በመቅረጽ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝም በምላሻቸው ተናግረዋል ፡፡

በቡናና ሻይ ልማት ስራዎች ምርትማነትን የሚያሳድጉ አሰራር ስርዓትን ተግባራዊ በማድረግ እንዲሁም የማሳ ሽፋንን የማሳደግ ስራ ተጠናክሮ ይሰራል ብለዋልም ፡፡

የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት አሁን ላይ መሻሻል ያሳየ ሲሆን በተገቢው ጥቅም ላይ በማዋል ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ይገባል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ከአፈር ማዳበሪያ ሽያጭ የተገኘ ገንዘብ በተገቢው በመሰብሰብ ወደ ባንክ ገቢ ማድረግ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡

የህብረት ስራ ማህበራትን አደረጃጀት በመፈተሸና አሰራራቸውን በማጠናከር ውጤታማ እንዲሆኑ በተገቢው ትኩረት ተሰጥቶት ይሰራበታል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል ፡፡

በከተማና በገጠር የሌማት ትሩፋት ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ የምክር ቤት አባላት ግንባር ቀደም ሆነው ሌሎችን በብዛት ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማስቻል የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡

የትምህርት ስብራትን ለመጠገን 161 ሚሊየን ብር ህብረተሰቡ ተሳትፎ በማድረግ በትምህርት ስራዎች ላይ ያሳረፈው አሻራ ሊመሰገን የሚገባውና ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ተግባር ነውም ብለዋል፡፡

በጤናው ዘርፍ በተለይም የወባ በሽታ ስርጭትን ለመቀነስ በተሰራው ስራ መሻሻሎች የታዩበት ተግባር መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል ፡፡ አሁን ላይ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የበለጠ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል ፡፡

በህገ ወጥ መድኃኒት ዝውውር ላይ የተጀመረው ቁጥጥርና ክትትል ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም በምላሻቸው ገልጸዋል ፡፡

በጤና ተቋማት ያለውን አገልግሎት አሰጣጥ በተገቢው በመፈተሽ ህብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ በትኩረት ሊሰራበት ይገባል ብለዋል ፡፡

ማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት ስራ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል ፡፡

በክልሉ ሰላምና ጸጥታ ስራዎችን ዘላቂ ለማድረግ በተሰሩ ስራዎች መሻሻሎች ዉጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን የገለጹት ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በድንበር አካባቢና በአርብቶ አደሩ አካባቢ አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ ጸጥታ ችግሮችን በቅንጅት የመቅረፍ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡

የገጠር የኮሪደር ልማት ስራዎች ከሌማት ትሩፋት ስራዎች ጋር በማስተሳሰር የሚሰራ ይሆናል ብለዋል ።

በመንገድ ልማት ስራዎች ጥገና አኳያ ከምክር ቤቱ አባላት በተነሱት ጥቄ ላይ የክልሉ መንግስት የጀመረውን ስራ አጠናክሮ የሚያስቀጥል መሆኑን ተናግረዋል ፡፡

የድልድይ እና የመንገድ ግንባታ ስራዎችን በተመለከተም ህብረተሰቡን በማሳተፍ የሚሰሩትን በማስተባበርና ከወረዳና ከዞን አቅም በላይ የሚሆኑትን ክልሉ መንግስት ደረጃ በደረጃ የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡

ህዝብ የሚነሳቸውን ልማት ፍላጎቶች የተሟላ አድርጎ ምላሽ ለመስጠት ክልላዊ ገቢ አሰባሰብ ስራዎችን ይበልጥ ማሳደግ ይገባናል ሲሉም ተናግረዋል ፡፡

በፌዴራል መንግስት እየተገነቡ ያሉ መንገዶች ተፈጻሚ እንዲሆኑ ከመንገዶች አስተዳደር ባለስልጣን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡

ህብረተሰቡን ንጹህ መጠጥ ዉሃ አቅርቦትና ተደራሽነትን ለማስፋት በመንግስትና በረጂ ድርጅቶች እየተሰራ ያለውን ስራ የማጠናከርና የማስቀጠል ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ፡፡

በንጹህ መጠጥ ውሃ ግንባታዎች በወጪ መጋራት የሚፈለገው ሀብት በተገቢው ተሰብስቦ ገቢ መደረግ እንደሚኖርበትም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል ፡፡

ማህበራዊ ቀውስ የሚፈጥሩ 32 ሺህ የሚሆኑ ሳይፈቀዱ የተያዙ የከተማ መሬቶችን በከተማ ሊዝ መነሻ መሰረት ህጋዊ የማድረግ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል ፡፡

የከተማ ኮሪደር ልማት ስራዎች አሁን ላይ ያለው ጅምር ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የማድረግ ስራዎችን ማከናወን ይገባል ሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ልማት ላይ የህብረተሰቡን ተሳትፎ ማሳደግ ይገባል ብለዋል ፡፡

የክልሉን ገቢ ከማሳደግ አኳያም በማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ አሰባሰብ ስርዓት ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት ሊሰራበት ይገባል ብለዋል ፡፡

የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭትን በተመለከተም በተለይ የቤንዚን አቅርቦትና ስርጭት በከተሞች ትልቅ ቀውስ እያስከተለ መሆኑን ያነሱት ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ልዩ ኦፕሬሽን በመስራት ህገ ወጥነትን ለመከላከል የተጀመረውን ስራ አጠናክረን እናስቀጥላን ብለዋል ፡፡

በክልሉ በኢኮኖሚ፣በማህበራዊ ልማት ስራዎች ውጤታማ ተግባራት ተከናውኗል።ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር)

በክልሉ ለወሳኝ ስራዎች ከተፈቀዱ ኬላዎች በስተቀር አልፎ አልፎ ሚታዩ ህገ ወጥ ኬላዎች ለህገ ወጥ አሰራር ምቹ በመሆናቸው የሚነሱበት ሁኔታ እንደሚፈጠርና ይህንም አድረገው የሚገኙ አካላት ተጠያቂ እንደሚሆኑም አሳስበዋል።

ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ከምክር ቤት አባላት በተነሱት አስቴየቶችና ጥያቄዎች ላይ በእነዚህና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ምክር ቤቱ የርዕሰ መስተዳደሩን ሪፖርት ካዳመጠ በኃላ በመሉ ድምጽ አጽድቋል።

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *