የኩባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ

Spread the love

የኩባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሩኖ ኤድዋርዶ ሮድሪጌዝ ፓሪላ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ሚኒስትሩ በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ ከመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል ሲል ኤፍኤም ሲ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *