




የፖለቲካና ሁለንተናዊ የልማት ስራዎች ለማሳለጥ አመራሩ ከመቼም ጊዜ በላይ በጊዜ የለንም መንፈስ መስራት አለበት ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ
በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ የፓርቲና የመንግስት ስራዎች ያለበት ደረጃ በተጨባጭ ወርዶ ለማረጋገጥና ለመደገፍ የማስፈጸሚያ ዕቅድ መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ሁሉንም የመልሚያ አማራጮችን በመጠቀም የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።
የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳድር ጥያቄዎች ለማድመጥና አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት በድጋፋዊ የሱፐርቪዥን ስራዎች ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወነ በመሆኑ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋለ።
እስካሁን በድጋፋዊ የሱፐርቪዥን ቡድን ወርዶ በመደገፍ ፣ የተሰሩ ስረዎችን ስቦ በመገምገም እና በቨርቸዋል የተቀናጀ ተስስር በመፍጠር ተግባራት ማከናወን ተችሏል።
ወንድማማችነት፣ እህትማማችነት እና አብሮነትን ለማጠናከር የድጋፋዊ የሱፐርቪዥን ተግባራት ሚናው የጎላ በመሆኑ ይህንን ተግባር ባህል እስኪሆን ድረስ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ እንዳሉት በክልሉ የድጋፍና የሱፐርቪዥን ስረዎች የአፈጻጸም ደረጃቸው ቢለያይም በሁሉም አካባቢዎች በፓርቲያችንና በመንግስት የተቀየሱ አዳዲስ የልማትና የመልካም አስተዳደር ትልሞችን ለማሳካት ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል።
በፓርቲያችን እሳቤዎች በብቃት በመተግበር ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ መትጋት አለብን።
የፓርቲያችን ኢኒሼቲቦችን ከግብ ለማድረስ አመራሩ በተጨባጭ መደገፍና በውጤት የታጀበ ስኬት ለማስመዝገብ በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።
በመድረኩ የገጠር ኮርደር ልማት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ እንደሚቀመጥ ተገልጿል።
