የሸካ ዞን ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

Spread the love

የሸካ ዞን ምክር ቤት 5ኛ ዙር 11ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 22ኛ መደበኛ ጉባኤውን በማሻ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።

ጉባኤውን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የሸካ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ዮሐንስ ካሳሁን ባለፉት ስድስት ወራት በዞኑ በርካታ የልማት የኢኮኖሚ እና የመልካም አስተዳደር ተግባራት በምክር ቤቱ ባሉ ቋሚ ኮሚቴዎች አማካይነት የሚከናወኑ የልማት ተግባራት ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገ ተጨባጭ ውጤት መመዝገቡን ጠቁመዋል።

በግብርናው ዘርፍ የቴክኖሎጂ ግብዓት አጠቃቀም ፣ የኩታ ገጠም እርሻ ሥራ፣የመሬት ሊኬት እንዲሁም ከሌማት ትሩፋት አንፃር የተመዘገበው ዝቅተኛ አፈፃፀም ለቀጣይ መታረም አለበት ያሉት ዋና አፈ ጉባኤው ከንግድ ስርዓቱ ጋር ተያይዞ በተለይ ከቤንዚን ጋር ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ምክር ቤቱ ተወያይቶበት አቅጣጫ እንዲያስቀምጥ ጠይቀዋል።

በከተማ ልማት በመሬት አቅርቦት፣በግብርናው በእንሴት ምርት፣ በትምህርትና በመንገድ ባለፉት ወራት የተሻለ አፈፃፀም መመዝገቡን ገልፀው ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠቁመዋል።

በጤናው ዘርፍ የወባ ወረርሽን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አኳያ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን ብሎም መከላከልን መሠረት ያደረገ ስራዎች የሁሉንም ርብርብ ይጠይቃል ብለዋል።

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ የመጣውን የህብረተሰብ ተሳትፎ በተለይ የመንገድ መሠረተ ልማት ስራዎች ላይ በሁሉም የዞኑ አካባቢዎች ሊጠናከር ይገባል ያሉት ዋና አፈ ጉባኤው ከአንድ መዋቅር የተወሰደው ልምድ በሁሉም ዘርፍ በለሎች መዋቅሮች ሊሰፋ እንደሚገባም በአጽንኦት አንስተዋል።

በጉባኤው የባለፈው ጉባኤ ቃለ -ጉባኤ መርምሮ ማፅደቅ፣የአስፈጻሚ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት፣የሸካ ማህበረሰብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ጣቢያ የእስካሁን አፈፃፀምና የቀሪ ወራት የጣቢያው ዕቅድ ቀርቦ ተገምግሞ የሚፀድቅ ሲሆን ምክር ቤቱ ሹመትን ጨምሮ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ አፈ ጉባኤው ጠቁመዋል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *