asc

Spread the love

የክልሉ ጤና ቢሮ ለአመያ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉ የሆስፒታሉን አገልግሎት አሰጣጥ ይበልጥ ለማሻሻል እንደሆነም ተነግሯል።

ድጋፉን ያስረከቡት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግሥት ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም እንደገለፁት ድጋፉ በሆስፒታሉ የሚሰጠውን የአገልግሎት አሰጣጥ ይበልጥ ለማሳለጥ እና በፌዴራል መንግሥት የተጀመረው የህንፃ ዕድሳት ስራ ሲጠናቀቅ ተጨማሪና አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን ቀድሞ ለማሟላት ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

ለሆስፒታሉ ድጋፍ ከተደረጉ ቁሳቁሶች መካከል የላቦራቶሪ ማይክሮስኮፕ፣ አልጋ፣ የአልትራሳውንድና የቀዶ ጥገና ቁሳቁሶችና ሌሎችም እንደሚገኙና አጠቃላይ ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ወጪ የወጣባቸው መሆኑን ገልፀዋል።

አያይዘውም የሆስፒታሉን ደረጃ ለማሳደግና አዳዲስ አገልግሎቶችንም ጭምር ለማስጀመር በዞኑ መንግሥት በኩል እየተደረገ ያለው ጥረት የሚበረታታና መጠናከርም ያለበት መሆኑን ጠቁመው መሰል ድጋፎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አክለዋል።

በርክክብ ወቅት የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም፣ የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ኡቴ አየለን ጨምሮ የሆስፒታል ስራ አስኪያጅና ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎችም ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን በመጨረሻም የህንፃ ዕድሳት ስራ ያለበትን ደረጃም ምልከታ ማድረጋቸዉን የዘገበው የኮንታ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *