የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 38ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመስተዳድር ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 38ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

በዚህም መሠረት፦

1ኛ.የ37ኛ መደበኛ ጉባዔ ቃለ ጉባዔን አፅድቋል።

2ኛ.በመቀጠልም የቀረቡ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት ጥያቄዎች ላይ ተወያይቷል። በዚህም የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን 9 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን መርምሮ በግብርና፣በእንዱስትሪና አገልግሎት የስራ ዘርፎች ለመሰማራት 527 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል መጠን በማስመዝገብ የቀረቡ ኢንቨስትመንት ጥያቄዎችን መርምሮ ወደ ስራ እንዲገቡ ወስኗል።

3ኛ. መስተዳድሩ ምክር ቤቱ በምርጥ ዘር ድርጅት፣በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን (ማዕጤመ) እና በኮሪደር ልማት ዙሪያም ተወያይቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *