በክልሉ የተጀመረውን ተስፋ ሰጪ የግብርና ልማት እንቅስቃሴን ወደ ላቀ ምዕራፍ ማሻገር ከባለድርሻ አካላት የሚጠበቅ ኃላፊነት መሆኑን የግብርና ቢሮ አስታወቀ ።

Spread the love

የክልሉ ግብርና ቢሮ ልማት አጋር አካላት ግንኙነት አማካሪ ካውንስል የምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተደረገ ነው።

በምክክር መድረኩ የተገኙት ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው የግብርና ልማት ዕድገትን በማፋጠን የህብረተሰቡን የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

በግብርናው ዘርፍ እየተመዘገቡ ያሉ ስኬታማ ተግባራትን ለማጠናከር የምርታማነት ዕድገት ማነቆ የሆኑ መሠረታዊ ችግሮችን ለይቶ እየፈቱ መሄድ ይገባል ብለዋል።

በዚህ ረገድ የግብርና ልማት አጋር አካላት ግንኙነት አማካሪ ካውንስል ሚናው የጎላ መሆኑንም አቶ ማስረሻ ተናግረዋል ።

በቀጣይ በጀት ዓመት የክልሉ የግብርና ልማት አጋር አካላት ግንኙነት አማካሪ ካውንስል በግብርና ምርታማነት ዕድገት ላይ ሚናቸውን በመወጣት ወደ ላቀ ምዕራፍ ለማሻገር ኃላፊነታቸውን በብቅት እንዲወጡም ጠይቀዋል ።

በምክክር መድረኩ የአማካሪ ካውንስል የተመለከተ ገለጻና የክልሉ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የሪፖርት እንዲሁም የ SNV ኢትዮጵያና የቴፒ ግብርና ምርምር ማዕከል ሰነዶች ቀርበዋል ።

በቀረቡት ሰነዶች ላይ ባለድርሻ አካላት እንደሚመክሩበት ታውቋል።

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *