


ከሶማሊላንድ ጋር በተደረገው ስምምነት ተፈጥሮ የነበረውን አላስፈላጊ ውጥረት ለማርገብ የተሰሩ ስራዎችን ቢብራሩ፤
የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ማሻሻያ ከመደረጉ በፊት ነባሩ የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር በኢኮኖሚያችን ላይ ያስከትላቸው የነበሩ ችግሮች ምን ነበሩ ቢያብራሩልን፣
ማሻሻያው በ2017 በጀት ዓመት የውጭ ምንዛሬ ግኝት ከማሳደግ አንፃር ምን አስተዋፅኦ አለው ተብሎ ይጠበቃል፣
የሃገራችን የፋይናንስ ዘርፍ ባለፉት ስድስት ዓመታት በሁሉም የአገልግሎት መስኮች ጥሩ ውጤት እያስመዘገበ እንደመጣ ተገልጿል፤ የዘርፉ የእስካሁን አፈፃፀም ቢያብራሩልንን፣
2017 በጀት ዓመትን ጨምሮ ለቀጣይ አመታት የፋይናንስ ዘርፍ ተወዳዳሪና ጤናማ ሆኖ እንዲቀጥል እንዲሁም አገልግሎቱን ለዜጎች በተገቢ ሁኔታ እንዲያቀርብ በመንግስት በኩል ምን ታቅዷል፣
ያልተፈቱ የህዝብ ጥያቄዎችን ከመመለስ አኳያ ምን ታስቧል፤ የህዝብ ማንነነት ከመመለስ አንፃር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቁጫ ህዝብና ራስ አስተዳደር የማንነነት ጥያቄ ማግኘት ላይ የርሰዎ ምላሽ ምንድን ነው፣
የሀገራችን ዜጎች በሀገራዊ ምክክር ሂደት ላይ በፍጹም ልበ ሙሉነት እንዲሳተፉ ለማድረግ ምን ታስቧል፣
ከኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር ተያይዞ ደመወዝ ማሻሻያው እስካሁን ተግባረዊ አልሆነም ለምን
የሥራ ፈላጊዎች ቁጥር እየጨመረ ቢመጣም በፌደራልና በክልል የተፈጠረውን የሥራ እድል በቋሚና በጊዜያዊነት ምን ያህ እንደሆነ ቢብራራ
ከቻይና ጋር ያለው ሁለትዮሽ ግንኙነት ከአለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ያለው አንድምታ ምንድነው፣
በሀገራዊ ምክክር ላይ ያለተሳተፉ አካላትን ለማሳተፍ ምን እየተሰራ ነው፣
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ። ይህን ተከትሎ ምክር ቤቱ የመንግስትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽኑን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
