ትውልዱ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ የሚገኙ የሰላምና ልማት ግንባታ ስራዎችን ማሳካት ይጠበቅበታል

Spread the love

ትውልዱ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ የሚገኙ የሰላምና ልማት ግንባታ ስራዎች ላይ በትጋት በመረባረብ የዘመኑ አርበኛ መሆን እንደሚጠበቅበት የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን ገለፁ።

129ኛው የዓድዋ ድል በዓል “ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል” በሚል መሪ ሀሳብ በዓድዋ ድል መታሰቢያ በተለያዩ መርሃ ግብሮች እየተከበረ ይገኛል።

በዚሁ ጊዜ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን እንደገለጹት፥ ጀግኖች አባቶችና እናቶች በወቅቱ የነበሩ የውስጥ ችግሮቻቸውን ወደ ጎን በመተው በአንድነት በመቆም የውጭ ወራሪ ሃይልን በማሸነፍ ደማቅ ታሪክ ጽፈዋል።

የአሁኑ ትውልድ ከዓድዋ ድል ተባብሮ መስራትን በመማር በአሁኑ ወቅት እየተካሄዱ ባሉ የልማትና የሰላም ግንባታ ስራዎች ላይ በንቃት በመረባረብና ከግብ በማድረስ የራሱን ድል ማስመዝገብ አለብት ሲሉም ገልጸዋል።

ትውልዱ እራሱን በትምህርትና በስነምግባር በማነጽ የሀገርን ኢኮኖሚ በመገንባት ተምሳሌት መሆን እንደሚጠበቅበትም እንዲሁ።

የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያውያን ባለፈ መላው የጥቁር ህዝቦች የሚኮሩበት ድል መሆኑንም አንስተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *