



በተያዘው የበልግ አዝመራ በዞኑ 6,659 ሄክታር ማሳ በአዲስ ተከላ መሸፈኑም ተመላክቷል።
እንሰት ስትራቴጂያዊ ሰብል ሆኖ እንዲወጣ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ የሸካ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አዕምሮ ደሳለኝ ገልጸዋል።
የመምሪያ ኃላፊው አክለውም በዞኑ በተያዘው የበልግ አዝመራ 6 ሺህ 659 ሄክታር ማሳ በአዲስ ተከላ መሸፈኑም ጠቅሰዋል።
አጠቃላይ ዞናዊ ሽፋኑን አሁን ካለበት 33 ሺህ 115 ሄ/ር ወደ 41 ሺህ 135 ሄ/ር በማሳደግ የምርታማነት መጠኑን በአንድ ሄክታር 300 ኩንታል ለማድረስ አቅዶ እየሰራ መሆኑን ገልጸው እስካሁን ለአዲስ ተከላ ከተዘጋጀው 20.05 ሚሊየን ችግኝ 16.65 ሚሊየኑ መተከሉን የመምሪያ ኃላፊዉ አስረድተዋል።
እንሰት ስትራቴጂያዊ ሰብል ሆኖ እንዲወጣ በምርምር የታገዘ አዳዲስ አሠራሮችን የመከተል፣ የተቀናጀ አሠራርን በማጎልበት በማሕበረሰብ ንቅናቄ የሰብል እንክብካቤ የበሽታ መከላከልና የመቆጣጠር ሥራን ማጠናከር እንዲሁም የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠትና ያልተቋረጠ የድጋፍና ክትትል ሥራ በትኩረት እንደሚሰራ አብራርተዋል።
በተጨማሪም ሥራውን ውጤታማ ለማድረግ አምስት የችግኝ ጣቢያዎችን አደራጅቶ ወደ ተግባር ማስገባት መቻሉን መምሪያው ኃላፊ መግለጻቸዉን የክልሉ ግብርና ቢሮ መረጃ ያመለክታል።
