የካፈቾ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል (የቤነ ሻደዬ ባሮ ) ለማክበር አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የካፋ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታወቀ

የካፋ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ
Spread the love

የካፋ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሀስያ አሊ የ2016 ዓ.ም የካፈቾ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል (የቤነ ሻደዬ ባሮ) አከባበርን አስመልክተዉ መግለጫ ሰጥተዋል።

ወ/ሮ ሀስያ በመግለጫቸው የካፈቾ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል ካፋ ህዝብ በንጉሣዊ ስረዉ መንግስት ዘመን ሲተዳደር ከነበረበት ጊዜ አንስቶ መከበር የጀመረ ታሪካዊ በዓል መሆኑን ተናግረዋል ፡፡

በዓሉ በታሪክም ንጉሱ የአመቱን የፓለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አፈፃፀም በመገምገም የተሻለ ስራ ያከናወኑትን ለተሻለ ሀላፊነት የሚያጩበት፤ ያጠፉትንም የሚገስፁበት ስርዓት ያለው በዓል እንደሆነ አንስተዋል።

በዓሉ የአርሶ አደሮች የአዝመራ አቆጣጠር ተከትሎ የሚከበር በዓል መሆኑን በመግለጽ አዝመራው ሲጠናቀቅ ሁሉም ህብረተሰብ ወደ ንጉሱ ዘንድ በመሄድ በጋራ የሚከበር በዓል ነዉ ብለዋል፡፡

የካፈቾ የዘመን መለወጫ በዓል ከንጉሡ ጊዜ በኀላ ለተወሰኑ ዓመታት ሳይከበር ተቋርጦ የነበረ ቢሆንም በዓሉ በመንግሥት ደረጃ ድጋሚ መከበር ከጀመረ ሃያ አመታትን አስቆጥሯል ብለዋል ወ/ሮ ሀስያ፡፡

በዓሉ በየጊዜው ታርካዊ ዳራውን ሳይለቅ ህላዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ ቀድሞ በነበረው ሂደት በየዓመቱ እንድከበር በርካታ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ኃላፊዋ ገልፀዋል፡፡

በዓሉ ሁሉም የካፋ ህዝብ በጋራ ያለምንም ልዩነትም የሚያከብሩበት ታርካዊ በዓል እንደሆነ የገለፁት ወ/ሮ ሀስያ የካፊቾ ዘመን መለወጫ በዓል አለም አቀፋዊ እውቅና አግኝቶ በዩኔስኮ እንዲመዘገብ የተለያዩ ጥናቶች እየተሰሩ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

የ2016 ዓ.ም የካፊቾ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓልን ለማክበር አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ጠቅሰው ለዚህም አብይና ንዑሳን ኮሚቴዎች ተቋቋመው የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ሲከናውኑ መቆየታቸውን አስረድቷል።

በዓሉ ከወረዳ ጀምሮ እስከ ዞን ድረስ በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበርም ተናግረዋል ።

የዘንድሮው የ2016 ዓ.ም የካፊቾ ዘመን መለወጫ በዓል በቦንጋ ከተማ ከመስከረም 12 እስከ መስከረም 13/2016 ዓ.ም ድረስ በፓናል ውይይትና በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች ታጅቦ በደማቅ ሁኔታ እንደሚከበርም ወ/ሮ ሀስያ ገልፀዋል ።

በበዓሉ ወቅት በክልላችን ያሉ የ6ቱም ዞን ተጋባዥ እንግዶች፣ ከአጎራባች ክልል ዉስጥ ያሉ መዋቅሮች ፣ በሌሎች አከባቢዎች የሚገኙ የካፋ ተወላጆች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች እንደሚሳታፉም ጠቁመዋል።

በዓሉ አለም አቀፋዊ እውቅና አግኝቶ በዩኔስኮ እንዲመዘገብ በሚደረገው ስራ እያንደንዱ የዞኑ ማህበረሰብ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ገልጸው በቦንጋ ከተማ የሚገኙ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ተቋሞቻቸውን በባህላዊ መንገድ በማሸብረቅ ባህላችንን ማጉላት አንደሚገባ ወ/ሮ ሀስያ አሳስበዋል፡፡

እያንደንዱ የከተማ ነዋሪዎች በዓሉን በሚያከብርበት ወቅት በህላዊ ስርዓቱንና የበዓሉ ሠላም በመጠበቅ ለበአሉ ድምቀት የበኩሉን መወጣት እንዳለበት ወ/ሮ ሀስያ ጥሪ አቅርበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *