




በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በ5 ዞንና በ 15 ከተማ አስተዳደሮች ተጨማሪ አገልግሎት እንደሚጀመርም ተገልጿል።
እንደ ሀገር በየዘርፉ የሚታዩ የአገልግሎት አሰጣጥ የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ የህዝቡን ምሬት አግዝፈወት ቆይተዋል።
መንግስትም ችግሩን ለመቅረፍ እና ለመፍትሄውም ” መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን “ወደ ስራ አስገብቷል ።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ብዝሀ ከተሞች ውስጥ አንዷ በሆነች ሚዛን-አማን ከተማ “መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት “ተከፍቶ ከጥቅምት 24/2018 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሰራ ገብቷል።
በማዕከሉ 35 አገልግሎቶች እየተሰጡ ሲሆኑ የክልል አምስት የፈዴራል 4 በድምሩ 9 ተቋማት በማዕከሉ እንደሚገኙ የማዕከሉ ስራ አስፈፃሚ አቶ አስራት አዳሮ ገልፀዋል።
ማዕከሉ ተከፍቶ አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በሁለት ወራት ውስጥ ከ13ሺ 439 በላይ ሰዎች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን አመልክተዋል።
የመረጃ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ሁሉም አገልግሎቶች ተፈላጊ ናቸው ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው ከዲጂታል መታወቂያ ጀምሮ የፖስታ፣የቴሌ ፣የገቢ፣የባንክ፣ በንግድ ዘርፍ እንዲሁ በጤና በኩል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተገልጋዮች መስተናገዳቸውን ተናግረዋል።
በተቋሙ የሚሰጠው አገልግሎት ዙሪያ መረጃ የሚሰበሰው በቀጥታ በበይነ መረብ ነው ያሉት ሀላፊው ከ97 በመቶ በላይ ተገልጋዮች እርካታቸውን የገለፁበት መሆኑን ተናግረዋል።
ቀደም ሲል አገልግሎት ፍለጋ ወደ ተለያዩ ቢሮዎች ይደረግ የነበረው መመላለስ እንዲሁም አላስፈላጊ የገንዘብ ወጪ እንዲሁም የጊዜ ብክነት ያስቀረ የክልሉ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መሆኑንም አመልክተዋል።
በማዕከል ተስተናግደው ሲወጡ ያገኘናቸው ተገልጋዮች ባለጉዳዮችን በተገቢው መንገድ ከመቀበል ጀምሮ የሚሠጡት የአግልግሎት ፈጣንና የተቀላጠፈ መሆኑ መስክረዋል።
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎ በሚዛን አማን ከተማ ላይ ታጥሮ የሚቀር ሳይሆን እየሠፋ የሚሄድ ሲሆን በቀጣይ በክልሉ 5 ዞኖችና በ15 የከተማ አስተዳደሮች አገልግሎቶቹ እንደሚጀመርም ዋና አስፈፃሚው ፤ አቶ አስራት አዳሮ አመልክተዋል ሲል ቤንች ሸኮ ቴቪ ዘግቧል።
