በክልሉ የቀጠለዉ የተ.መ.ድ ከፍተኛ አመራሮች ጉብኝት

Spread the love

ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሥራ ኃላፊዎች ለሥራ ጉዳይ ወደ ታርጫ ከተማ ገቡ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እና ሰሞኑን በክልሉ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሥራ ኃላፊዎችና ተወካዮች በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት በዳዉሮ ዞን ታርጫ ከተማ ገብተዋል።

ወደ ታርጫ ከተማ ከገቡት የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች መካከል የዓለም ጤና ድርጅት (WHO)፣ የምግብና ግብርና ድርጅት (FAO)፣ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (UNIDO)፣ የሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ቢሮ (OCHA) እና ሌሎች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሥራ ኃላፊዎችና ተወካዮች ይገኙበታል።

የተባበሩት መንግስታት የሥራ ኃላፊዎችና ተወካዮች ወደ ታርጫ ከተማ ሲደርሱ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ፣ የታርጫ ከተማ ከንቲ አቶ አስናቀ አበበ ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የዞንና የከተማ መንግስት ሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የልማት አጋሮቹ በከተማ በሚኖራቸው ቆይታ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *