



የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የመስኖና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ምርታማነት ጉባኤ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ከየካቲት 5 እስከ 7 ቀን 2017 ዓ.ም በሚካሄደው በዚህ ጉባኤ የዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ መሪዎችና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ይሳተፉበታል ተብሏል።
የጉባዔው ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ዝግጅት ማስጀመሪያ መርኃ ግብር ዛሬ ተካሂዷል።
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትሩ አብርሃም በላይ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት በጉባዔው የኢትዮጵያ የመስኖ ልማት ልምድና ተሞክሮዋን ታቀርባለች።
አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉባዔዎችን በተሳካ መልኩ በማስተናገድ ተመራጭ የሆችው ኢትዮጵያ፤ ይህን ጉባዔ በተሳካ መልኩ ለማስተናገድ ዝግጅት ማድረጓን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ የውሃ ሃብት፣ ለመስኖ ልማት የሚውል ምቹና ሰፊ መሬት፣ የማዕድናትና ሌሎችም ፀጋዎች በስፋት ለማልማት እየተሰራ ነው።
የሌማት ቱሩፋት፣ የበጋ መስኖ የስንዴ እና የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከኢትዮጵያ ስኬቶች መካከል ይጠቀሳሉ።
ለዚህም መንግስት የፖሊሲ፣ የአደረጃጀት እና የአሰራር ማሻሻያ እርምጃዎችን በማድረጉ የተገኘ ስኬት መሆኑ ይታወቃል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
