በቴክኖሎጂ የታገዘ የመንግሥት የግዥ ስርዓት ተግባራዊ በማድረግ የሀብት ብክነትን መቀነስ ይገባል። ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

Spread the love

የኢፌዲሪ የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን በመንግሥት የኤሌክትሮኒክ ግዥ ሥረዓት አተገባበር ዙሪያ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር በቦንጋ ከተማ ውይይት እያደረገ ይገኛል።

በምክክር መድረኩ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እንደገለጹት፥ በቴክኖሎጂ የታገዘ የመንግሥት የግዥ ስርዓት ተግባራዊ በማድረግ የሀብት ብክነትን መቀነስ ይገባል ብለዋል።

የኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓት ውስን የኾነውን የህዝብና የመንግሥት ሀብት በተገቢው ከማስተዳደር ባለፈው በግዥ ስርዓት ሂደት ውስጥ ፍትሀዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ስረዓት እንደሆነ ገልጸዋል።

በክልሉ የሚከናወኑ የመንግሥት የንብረትና የአግልግሎት ግዥዎችን በቴክኖሎጂ በተጋዘ መልኩ በማሳለጥ የጊዜና የሀብት ብክነትን ለመቀነስ የክልሉ መንግሥት በቁርጠኝነት አንደሚሰራም ርዕሰ መስተዳድሩ የገለጹት።

በመድረኩ የተገኙት የኢፌዴሪ የግዥና ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መሠረት መስቀሌ የመንግሥት የኤሌክትሮኒክ ግዥ ሥርዓት (ኢጂፒ) አስፈላጊነትና ጠቀሜታዎች እንዲሁም ዝርዝር አፈጻጸም ዙሪያ ገለጻ እየሰጡ ይገኛል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *