ምክር ቤቱ 4ኛ ዙር 12ኛ ዓመት የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤ ማካሄድ ጀመረ።

Spread the love

የቤንች ሸኮ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 12ኛ ዓመት የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤ ማካሄድ ጀምሯል።

ምክር ቤቱ በመደበኛ ጉባኤው የምክር ቤቱን ጨምሮ የአስፈጻሚ አካላት የመጀመሪያ ግማሽ አመት ዕቅድ አፈጻጸም ለምክር ቤቱ ቀርቦ ተገምግሞ ይፀድቃል ተብሏል።

ጉባኤው ለ2 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የምክር ቤቱ መደበኛ ጉባኤ የልማት ስራዎች ጉብኝት ጨምሮ ልዩ ልዩ ሹመቶችንም እንደሚያጸድቅ ከወጣው መርሃ ግብር ማወቅ ተችሏል።

በጉባኤው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ፣ የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን ጨምሮ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮችና ማናጅመንት አካላት መገኘታቸዉን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *