የብልፅግና ወጣቶች ክንፍ የስያሜ ለውጡን ይፋ አደረገ

Spread the love

የብልፅግና ወጣቶች ክንፍ ባለፈው ወር በፓርቲው 2ተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በተቀመጡ አቅጣጫዎች ዙሪያ እየመከረ ይገኛል።

በአዳማ ከተማ በመካሄድ ላይ የሚገኘው የብልፅግና ወጣቶች ክንፍ ምክር ቤት በፓርቲው ጉባኤ በተወሰነው መሰረት የአደረጃጀቱ መጠሪያ የወጣቶች ሊግ ከነበረበት የወጣቶች ክንፍ ተብሎ ጥቅም ላይ እንዲውል አቅጣጫ ሰጥቷል።

ምክር ቤቱ ሶስት አጀንዳዎችን ማለትም ፦ የ6ወራት አፈፃፀም ግምገማ፣ በመላው ሀገሪቱ የወጣቱን ተጠቃሚነት አስመልክቶ የተካሄደውን ሱፐርቪዥን ሪፖርት መገምገምና የጉባኤዉን ዉሳኔዎች አተገባበር አስመልክቶ በአጀንዳነት ያቀረበ ሲሆን አጀንዳዎቹ በምክር ቤቱ በሙሉ ድምፅ ፀድቀው እየተመከረበት ይገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *