Trendings

ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ የአያሌው ህይወቴ የወተት ላሞች እርባታ ጎበኙ

Spread the love

አቶ አያሌው የወተት ምርታማነትን ለማሻሻል የተሟላ ፓኬጅ በመጠቀም እየሰሩ እንደሚገኙ ተገልጿል ።

አቶ አያሌው ካላቸው 16 ላሞች በቀን 80 ሊትር ወተት ለህብረተሰቡ እንደሚያቀርቡም ተናግረዋል።

በአማካይ ከአንድ ላም በቀን 15 ሊትር ወተት እንደሚገኙ ገልጸዋል።

በጉብኝቱም የተጀመረው ስራ የሚበረታታ መሆኑንና ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል ።

ከርዕሰ መስተዳድሩ ጋር ዋና አፈጉባዔ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ፣ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸዉን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣የሸካ ዞንና የቴፒ ከተማ አስተዳደር አመራሮች በጉብኝቱ ተገኝተዋል።

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *