

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በጽ/ቤታቸው አማካኝነት በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ የሚገነባውን የአረጋውያን ቤት ግንባታ አስጀምረዋል።
የአካባቢው ማኅበረሰብ በክረምት በጎ ተግባር ላይ የጉልበት የቁሳቁስ ድጋፍ እንዲያደርጉ ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል።
የክረምት ወራት በጎ ተግባር ከጊዜ ወደ ጊዜ በስፋት እየተለመደ የመጣ ባህል መኾኑን የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ ካለው ላይ በማካፈል እንዲሁም ደጋፊ ያጡ አረጋውያንን መደገፍ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
በጽ/ቤቱ በኩል የሚገነባው የአረጋውያን ቤት ግንባታው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እንደሚሰራም ተገልጿል።
በክልሉ በ2017 ክረምት 636 የአዲስ የአረጋውያን ቤት ግንባታ እና የ410 ቤት ጥገና ስራ እንደሚከናወን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።
በማስጀመሪያ መርሀግብሩ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፌ-ጉባኤ ወንድሙ ኩርታ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸውን ጨምሮ ሌሎች የክልል እና የሸካ ዞን የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በዕድገቱ በዛብህ
