






የሀገር ውስጥ የሥራ ስምሪቱን ከማስፋትና ከማዘመን በሻገር ዓለም አቀፍ የሥራ ገበያው ያለውን ዕድል አሟጦ ለመጠቀም በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ።
በ5ኛው ሀገር አቀፍ ብሔራዊ የሥራ ኤክስፖ አፈፃፀምና የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል እና የሥራ፣ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሰለሞን ሶካን ጨምሮ የደረጃ ዶት ኮም እና የኢትዮ ጆብስ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የቀጣሪ ድርጅቶችንና የተቋማትን ውጤታማነት የሚያልቁ ሥራ ፈላጊዎችን የማገናኘቱን ሥራ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ተመላክቷል።
በውይይቱ የሥራ ፈጠራ ስነ-ምህዳሩን ማስፋት የሚያስችሉ ጉዳዮች በዝርዝር ቀርበዋል።
በዚህም ቀጣሪ ድርጅቶችንና የተቋማትን ውጤታማነት የሚያልቁ ሥራ ፈላጊዎችን የማገናኘቱ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠቁሟል፡፡
የሀገር ውስጥ የሥራ ስምሪቱን ከማስፋትና ከማዘመን በሻገር በዓለም አቀፍ ደረጃ የርቀት የሥራ መስክን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ያሉ እድሎችን አሟጦ ለመጠቀም እንደሚሰራም ተገልጿል፡፡
በዚህም የግሉ ዘርፍ ሚናውን እንዲወጣ የማስቻል፣ማነቆዎችን በመፍታት እና ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ዜጎችን ጥራት ያለው የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ መገለጹን ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመለክታል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
