





በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ሀብት አፈራለሁ፤ የሀገሬን ሰላም እጠብቃለሁ ፣የኢትዮጵያን ብልጽግና አፋጥናለው ” በሚል መሪ ሀሳብ በቦንጋ ከተማ ከወጣቶች ሊግ አባላትና ደጋፊዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል።
በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ወጣት ፍቃዱ ሀጥያ የወጣቶችን ዘለቄታዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሠላም የሁሉም ነገር መሰረት መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም አብሮነታችንን በማጠናከር፤የሀገራችንን ሰላም በማስጠበቅ ለትውልድ የሚተርፍ ምንዳ ለመፍጠር ወጣቱ በተሰማራበት መስክ ሁሉ አርአያ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።
ሁሉን አሰባሳቢ የብሔራዊነት ገዢ ትርክትን ለማጽናት
ወጣቶች ሀላፊነታቸው መወጣት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል ።
ከአገራዊ ለውጡ በኃላ ህዝቡን ያሳተፈ የዴሞክራሲ ስርዓት እንዲገነባ ወሳኝ ርምጃዎች የተጀመሩ መኖሩን የገለጹት ወጣት ፍቃዱ እነዚህ ጅምር ለውጦች ተጠናከረው ኢንዲቀጥሉና ዘላቂ ሰላም ኢንዲረጋገጥ የትምህርት፤ የሀይማኖት፤ የሚዲያና የሲቪክ ማህበራት ተቋማትን ሰላም በማስተማር የበኩላቸው ድርሻና ሃላፊነት እንዲመጡ ወጣቱ በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚገባ ጠቅሰዋል።
ብሔራዊ መግባባት እና ጠንካራ ሀገርን በመገንባት ሂደት ውስጥ ወጣቶች ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ያሉት የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት ወጣት የኔወርቅ ገለፍቶ ናቸው።
የሀገራችንን ብልጽግና ለማረጋገጥ ሀብት በመፍጠር፤ አብሮነታችንን በማጠናከር ሂደት ውስጥ የወጣቶች ሚና ጉልህ እንደሆነ የገለጹት ወጣት የኔወርቅ ጊዜን በአግባቡ በመግራት በየአከባቢያቸው ያሉትን ሀብትና ፀጋዎች በፈጠራ እና በፍጥነት አልምቶ የመጠቀምና የማስተዳደር ሀገራዊ ሀላፊንት አለብን ብለዋል።
የወጣቱን በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በትብብር እና በአንድት መስራት ይኖርብናል ብለዋል።
የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ወጣት ሙሄድን አህመድ እንደገለጹት በርካታ የሚያስተሳስሩን ድልብ ማህበራዊ ሀብቶቻችን ላይ ወጣቱ አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት ጠቅሰዋል።
የሀገራችንን ብልጽግናም ማረጋገጥ የምንችለው ወጣቶች የሀገራችንን ሰላም በማስጠበቅ፤ አብሮነትን በማስረፅና ለሀገር እድገት የበኩላችንን ሚና ስንወጣ ብቻ እንደሆነ አመላክተዋል።
በዚህም ሁሉንም አካታች ያደረገ ብሔራዊ ምክክር ማድረግ እና ልዩነቶቻችን ማጥበብና የጋራ መፍትሄ ማስቀመጥ ስንችል በመሆኑ ሀገራዊ ምክክሩ የተሳካ እንዲሆን ተገቢውን ጥረት ማድረግ ይኖርብናል ሲሉ አስረድተዋል።
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የዲሞክራሲና ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ግርማ ባሻ በሰጡት አስተያየት ሰላም፣ልማትና ብልጽግናን ለማረጋገጥ የወጣቱ አይተኬ ሚና እንዳለው ገልጸዋል። የወጣቱን ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት ላይ በትብብር መስራት ከሁሉም ይጠበቃል ብለዋል።
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት የፖለቲካና አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ወንዱ መንገሻ በሰጡት አስተያየት በክልሉ የመገኙ ወጣቶች ከክልል መስረታ ጀመሮ በሁሉም የልማት መስኮች ላይ አርአያነት ያለው ተግባር በመፈጸም የመሪነት ሚናቸውን ተጫውተዋል ብለዋል።
ወጣቱ የመሪነት ሚናውን አጠናክሮ በማስቀጠል ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሁሉም ዘርፎች እመርታዊ ውጤት ለማስመዝገብ መትጋት እንደሚያስፈልጋል ጠቅሰዋል።
