






በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሚገኙ የህብረት ስራ ማህበራት የስራ እንቅስቃሴ የሚያሳይ እንዲሁም ምርትና አገልግሎታቸውን የሚያስተዋዉቅ የፎቶ አውደ ርዕይና ኤግዚቢሽን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ መርቀው ከፍተዋል።
በሚዛን አማን ከተማ “የህብረት ስራ ማህበራት ለኢትዮጵያ ብልጵግና” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ በሚገኘው የህብረት ስራ ማህበራት ረፎርም ንቅናቄ መድረክ ተሳታፊዎች የፎቶ አውደ ርዕይና የማህበራት ምርት የሚያስተዋዉቅ እግዚቢሽን ተዘዋዋዉረው ተመልክተዋል።
በመረሃ ግብሩ በክልሉ ካሉት ከስድስቱ ዞኖች የተወጣጡ አስራ አምስት የህብረት ስራ ማህበራት ምርትና አገልግሎታቸውን አቅርበዋል።
ይህም ማህበራት ያላቸው ምርትና አገልግሎት እንዲያስተዋዉቁ ፤ ዘላቂነት ያለው የገበያ ትስስር እንዲፈጠርላቸውና እርስ በእርስ ምርጥ ተሞክሮ እንዲቀምሩ እንዲሁም የማህበራትን አቅም እንዲያጠናክሩ ጠቀሜታ ጉልህ መሆኑም ተገልጿል።
በፍቅር ከበደ
