የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና የጽ/ቤቱ ኃለፊ አቶ አደም ፋራህ፣የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈጉባኤ ፣ የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈጉባኤ ፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና ሚኒስትሮች የኮይሻ የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታ ሥራን ጎብኝተዋል።
በአፍሪካ ደረጃ በግዙፍነቱ ሶስተኛ ደረጃ የሆነዉን የኮይሻ ግድብ የንፁህ የኃይል ማመንጨት ስራችንን ያለበት ደረጃ አበረታች መሆኑን አመራሮቹ በምልከታቸዉ አይተዋል።
በጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ በቅርብ ርቀት የሚገኘዉ የኮይሻ ግድብ ለሀገራችን ተጨማሪ የኢኮኖሚ አቅምና የመልማት ዕድል የሚፈጥር ነዉ።
በግንባታ ሂደትም ለበርካቶች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል እየፈጠረ ይገኛል::
