ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በሚዛን አማን ከተማ እየተሰራ ያለውን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ግንባታ ያለበትን ደረጃ ጎበኙ።



መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ሲጠናቀቅ የመንግስት አገልግሎትን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያቀላጥፍ መሆኑም ተጠቅሷል ፡፡
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ሽግግር ውስጥ ያለው ድርሻ የላቀ ነው፡፡
ማዕከሉ ይኸንኑ እውን ለማድረግ በክልሉ ሚዛን አማን ከተማ ላይ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰራ ይገኛል ።
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከል ግንባታዉ የደረሰበትን ደረጃ ምልከታ ለማድረግ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በሚዛን አማን ከተማ ተገኝተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በስፍራው ተገኝተው በሰጡት አስተያየት የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ማስጀመር ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ያግዛል ብለዋል።
የማዕከሉ ግንባታ ተጠናቅቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር የህዝብና የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ያዘምናልም ብለዋል።
የጠቅላይ ሚነስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ኢኒሼቲቭ አካል የሆነው ይህ የሚዛን አማን ማዕከል የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ የንግድና ኢንቬስትመንት ፣ የገቢ አገልግሎቶችን ለመስጠት የሚያስችል ስለመሆኑም ገልጸዋል።
ማዕከሉ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር የህዝብ ቅሬታዎችን ለመፍታት፣ ሌብነትና ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል እና ተጠያቂነትን ለማስፈን ያግዛልም ብለዋል።
ማዕከሉ የተቀናጀ አገልግሎት ለተገልጋዩ መስጠት የሚያስችል ትልቅ ውጤታማ ስራ መሆኑንም ገልጸው፤ ማዕከሉን በማደራጀት ወደ ስራ ማስገባቱ በሀገሪቱ የታለመውን ድጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡
ማዕከሉ ቅሬታ ይቀርብባቸው የነበሩ አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል በማስገባት የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
በማዕከሉ የቴሌኮሙኒኬሽን ፣የባንክ አገልግሎት ፣የፋይዳ መታወቂና የመንጃ ፈቃድ አሰጣጥ አገልግሎት እንደሚሰጥም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል ።
ማዕከሉ በቅርቡ ተጠናቅቆ አገልግሎት መስጠት እንዲችል የክትትልና ድጋፍ ስራው ይጠናከራልም ብለዋል።
በክልሉ የተጀመረው የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከላት በሌሎችም እንዲስፋፋ ይደረጋልም ብለዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በጉብኝታቸው የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ህንጻ ግንባታና የተቋማት አገልግሎት አሰጣጥን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
በጉብኝቱ ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ የክልል እና የዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/
