



ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ባቀረቡት የአስፈጻሚ ተቋማት ሪፖርት በአርብቶና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች በተሰሩ ስራዎች ተጨባጭ ለውጦች መገኘታቸውን አብራርተዋል ፡፡
175 የአርብቶና ከፊል አርብቶ አደር ልጆች በክልሉ ባሉ 2 ሆስቴሎች የሆስቴል አገልግሎቶችን አግኝተው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ተደርጓል ፡፡
በመጀመሪያ ዲግሪ መርሐ ግብር 116 ተማሪዎች ፣ በዲፕሎማ 37 ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ተደርጓል ፡፡
ከመሰረተ ልማት ተቋማት ግንባታ አንጻር የ4 ጥልቅ ውሀ ጉድጓድ ቁፋሮ ቦታ ልየታ የጥናት ስራዎች ተጠናቀዋል ፡፡
በሜኤኒት ሻሻ ወረዳ ኪሉ ቀበሌ፣ በሜኢኒት ጎልድያ ወረዳ ዜማ እና ጎማ ቀበሌ በድምሩ 3 ጥልቅ ውሀ ጉድጓድ ቁፋሮ 33.3% ደርሷል ፡፡
የኡፊት ት/ቤት ግንባታ 97% ላይ የሚገኝና ቀጣይ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ቀሪ ክፍያ በመፈጸም የግንባታዉ ርክክብ የሚደረግ ይሆናል፡፡
በመንገድ ልማት ስራ የመንገድ ችግር የሚታይባቸዉን አካባቢዎች ቅድሚያ በመስጠት በ6 የመንገድ ጥናትና ዲዛይን 290 ኪ/ሜ ዲዛይን ሥራ ተከናውኗል፡፡
በመንገዶቹ ላይ የሚገኙ 12 የድልድይ ጥናትና ዲዛይን (ጋራ፣ ቱርጋ፣ ነዳ፣ ናቡር እና ሹላ፤ ቡሮ ድልድይ፤ ማሙሩ፣ ዴካ፣ ሾሻሮ፣ ሹሪ፣ እና ኩጃጉዱ፤ ቱልጊት እና ሞጋ) ድልድይ ስራዎች በማጠናቀቅ የዲዛይን ሰነድ ርክክብ ተደርጓል።
ከባቹማ እስከ ጨበራ 18 ኪ/ሜ የጠጠር መንገድ ግንባታ 70% ደርሷል፡፡
የዳል ወንዝ መካከለኛ ድልድይ ግንባታ 100% ግንባታው ተጠናቆ ጊዜያዊ ርክክብ ተከናውኗል፡፡
የኪሉ ወንዝ መካከለኛ ድልድይ ግንባታ 50% ደርሷል ፡፡
ከከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ስራዎች አኳያ በመሬት ልማትና ማኔጅመንት ለተለያዩ ዘርፎች 508 ሄ/ር መሬት በሊዝ መነሻ ዋጋ በምደባ 125 ሄ/ር በግልጽ ጨረታ ተላልፈዋል፡፡
በከተሞች ሳይፈቀድ የተያዙ 32,600 ይዞታዎችን ህጋዊ ስርዓት ለማስያዝ ምዝገባ ማከናወን ተችሏል፡፡
ለ1,680 ይዞታዎች ማረጋገጫ ተሰጥቷቸዋል፡፡
ከአገልግሎቱም 24,478,958.5 ብር ገቢ ማግኘት ተችሏል ፡፡
በመንግስት የማይሸፈኑ ሥራዎችን ህ/ሰቡን በአደረጃጀት በማነቃነቅ የልማቱ ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ ለመሠረተ ልማት ግንባታ 32,564,605 የሀብት ድጋፍ በማሰባሰብ ለከተሞች ልማት እንዲውል ተደርጓል፡፡
በቤት ልማት ፕሮግራም ተደራጅተዉ ቁጠባቸውን ላጠናቀቁ ለ109 ማህበራት 22.8 ሄ/ር መሬት በማስተላለፍ 1362 ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡
የከተሞችን ፈርጅ ወይም ደረጃ ከማሻሻል አንጻር በፈርጅ አራት 4 ከተሞች (ማዝ፣ ጌንጃ እና ኩጃ ፣ ባሺ፤ ወደ ፈርጅ ሁለት 1 ከተማ (ታርጫ) እንዲሁም ወደ ፈርጅ አንድ 2 ከተሞች (ቦንጋ እና ሚዛን አማን) ማሸጋገር እንደተቻለ አብራርተዋል፡፡
በታጠቅ አበበ
