የክልሉ ንጹህ መጠጥ ውሃ ሽፋንን ከ42.8 ከመቶ ማድረስ ተችሏል ፡፡ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ፡፡

Spread the love

ርዕሰ መስተዳድሩ ለክልሉ ምክርቤት ባቀረቡት የ2016 በጀት ዓመት አፈጻጸም የክልሉ ንጹህ መጠጥ ውሃ ሽፋንን ከ42 በመቶ በላይ ማድረስ ተችሏል ብለዋል ፡፡

በዚህም ፡- የክልሉን የንጹህ መጠጥ ውሃ ከማሳደግ አኳያ የተሰሩ ስራዎች

በክልሉ ካፒታል 4 ነባር ፕሮጀክቶች ግንባታቸው በጥሩ ሂደት ላይ ነው ፡፡

የተቺቢ ንጹህ መጠጥ ዉሃ ግንባታ አፈፃፀም 80%፣ የቦባ ጌጫ 78%፣ የእርምጭ ኩቢጦ አዲስ አለም የመጀመሪያ ምዕራፍ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት 99%፣ የማዝ ቀበሌ የንጹህ መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክት ግንባታ አፈፃፀም 86.67% ደርሷል፡፡

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በጀት ድጋፍ የቦንጋ ከተማ የንጹህ መጠጥ ዉሃ ማስፋፊያ ግንባታ ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ 13,200 የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ ሆነዋል።

በባስኬት ፈንድ ፕሮግራም 3 ፕሮጀክቶች በዕቅድ ተይዘው እየተሰሩ ይገኛሉ ፡፡

የዋቻ ከተማ የንጹህ መጠጥ ዉሃ ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ 36,000 የከተማ ነዋሪዎች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

ያሎ ላላ ከተማ የንጹህ መጠጥ ዉሃ ግንባታ ፕሮጀክት ፊዝካል አፈጻጸም 85% ፣የቱም ከተማ የንጹህ መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክት ፊዝካል አፈጻጸሙ 98% ደርሷል ፡፡

በዘላቂ የልማት ግቦች ማሳኪያ /SDG/ 11 ፕሮጀክቶች ግንባታቸዉ እየተከናወነ ነው ፡፡የኮንታ ኮይሻ መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክት 50%፣ የከጪ ከተማ ንጹህ መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክት 75%፣ የካካ ከተማ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ወደ 30%፣ የግዝ መሬት ከተማ ንጹህ መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክት 80%፣ የሻይ ምንጭ ግንባታ 98%፣ የቻይት እና ኦሚያ መጠጥ ውሃ ግንባታ ስራ 40% ደርሰዋል ፡፡

በዋሽ ምዕራፍ ሁለት ፕሮግራም የ13 ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ ነው ፡፡

ከዚህም ውስጥ የበዳውሮ ዞንና በሸካ ዞን ገቲባ የንጹህ መጠጥ ዉሃ ግንባታ ፕሮጀክቶች ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቀዋል ፡፡

በታርጫ ከተማ 24,523 ነዋሪዎች፤ በአንድራቻ ወረዳ የጋቲባ ከተማ ንጹህ 3,060 ነዋሪዎች ተጠቃሚ ሆነዋል ፡፡

በካፋ ዞን ሳይለም ወረዳ ሹንጋ ቀበሌ የንጹህ መጠጥ ዉሃ ግንባታ ፕሮጀክት 80%፣

በሸካ ዞን የማሻ ከተማ ንጹህ የመጠጥ ዉሃ የጨረታ ሂደት በማጠናቀቅ 20% ማድረስ ተችሏል፡፡

በጥልቅ የጉድጓድ ውሃ ቁፋሮ ከተያዙ 6 ፕሮጀክቶች ዉስጥ በካፋ ዞን ወሺ 90%፣

በኪዮ 100% እና የኩሻንታ ጥልቅ የዉሃ ጉድጓድ 90% ደርሰዋል ፡፡

በዩኒሴፍ ፕሮግራም 5 ፕሮጀክቶች ግንባታቸዉ እየተከናወነም ይገኛል ፡፡

በሰሜን ቤንች ወረዳ የጌንጃ መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክት እንዲሁም በዛባ-ጋዞ ወረዳ የደቼ ደነባ ቀበሌ መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክት 100% ደርሰዋል ፡፡

በዚህም 2,500 የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡

በቤሮ ወረዳ ሾላ ቀበሌ የንጹህ መጠጥ ዉሃ ግንባታ 20%፣ በአዲዮ ወረዳ አንጊዮ ቆላ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት 50%፣ በሸኮ ወረዳ የቦይታ ቀበሌ ንጹህ የመጠጥ ዉሃ ፕሮጀክት 75% ደርሰዋል፡፡

የክልሉን የመጠጥ ውሃ ሽፋን በአማካይ በገጠር ከነበረበት 38.7% ወደ 39.72%፣

በከተማ በአማካይ ከነበረበት 46% ወደ 59.0%፣ በማድረስ ክልላዊ የመጠጥ ውሃ ሽፋን በአማካይ ከነበረበት 39.8% ወደ 42.8% ማድረስ መቻሉን በሪፖርታቸዉ አመላክተዋል።

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *