ርዕሰ መስተዳደሩ ሪፖርታቸዉን ማቅረብ እንደቀጠሉ ነዉ

Spread the love

1. የማህበራዊ ልማት ሥራዎች አፈፃፀምን በሚመለከት

➣ ህብረሰቡን በማስተባበር በብር 65,361,160 ብር በማሰባሰብ በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የተዘጋጁ የመማሪያ ማሰተማሪያ መጽሃፍትን በማሳተም ተደራሽ ማድረግ ተችሏል፡፡

ከ1ኛ-6ኛ እንግሊዘኛ መፅሀፍት በቁጥር 104,000 በክልሉ መንግስት በ21 ሚሊዮን ብር በማሳተም ወደ ዞኖች እና ት/ቤቶች ተሰራጭቶ ለመማር ማስተማር ስራ እንዲውሉ ተደርጓል፡፡

➣ በትምህርት ለትዉልድ ንቅናቄ ስራ 414,704,720 ብር በመሰብሰብ 551 የነባር መማሪያ ክፍሎች ጥገና፤ 8 ቤተ መፅሀፍት ግንባታ፤ የተለያዩ የትምህርት ቤት ግብዓቶችን ማሟላት ተችሏል፡፡

➣በ2016 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ወደ ትምህርት ገበታ ከሚመጡ ተማሪዎች 12,241 ተማሪዎች ምገባ አግልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡

➣ ለ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ በኦንላይን እና ኦፍ ላይ በክልሉ ከ 4ሽህ በላይ ተማሪዎች ፈተናዉን ወስደዋል፡፡

➣ የተቋማዊ አቅምና ብቃት ማሳደግ በሚመለከት በደረጃ A እና B በድምሩ 1089 አሰለጣኞችን ማፍራት ተችሏል፡፡

➣ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተደራሽነትና፣ ፍትሐዊነትን በማሳደግ በአዲስና ነባር መደበኛ እንዲሁም በአጫጭር ሥልጠና የቅበላ አቅም ማሳደግ ተችሏል፡፡

➣ ለኢንተርፕራይዞች የተሟላ የኢንድስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ በማኙፋክቸሪንግ፣በኮንስትራክሽን እንዲሁም በአገልግሎት ዘርፍ ለነባርና ለአዳዲስ ኢንድስትሪዎች ድጋፍ መስጠት ተችሏል፡፡

➣ በክልሉ የቴክኒክና ሙያ የግንባታ ፕሮጀክቶች መካከል ቀድሞ የተቋረጡ /አዉራዳ ና ያዶታ / በጨረታ ወጥቶ ለተቋራጮች ርክክብ ተደርጎ ግንባታቸዉ በጥሩ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሲሆን በቀጣዩ የስልጠና ዓመት አሁን ስልጠና ከሚሰጥበት መደበኛ ትምህርት ቤት በራሳቸዉ ግቢ ስልጠና የሚጀምሩበት ሁኔታ ለመፍጠር በትኩረት እየተሠራ ይገኛል፡፡

➣ በሌላ በኩል የጪዳ እና ባቹማ ሥራ ተቋራጩ በዋጋ ማሽሽያው ባለመስማማታቸዉ የኮንትራክት አግባቡን ተከትሎ ውለታ እንዲቋረጥ በሌሎች አማራጮች በአዲሱ በጀት ዓመት ወደ ሥራ እንዲገባ ምክክር እየተደረገ ነው፡፡

➣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የመንግስታዊ ተቋማት የመረጃ ልዉዉጥ ለማቀላጠፍ እንዲጉም ደህነታቸዉን በማረጋገጥ የኢኮቴ ግብዓት በማመሟላት የቨዲዮ ኮንፍራንስ/ ዙም ሚትግ/ አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ ተችሏል፡፡

➣ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲን በመደበኛ ስልጠና የምዘና ብቃት ማረጋገጥ እንዲሁም አዳዲስ የምዘና ጣቢያዎችን ከማፍራት መቻሉን፡፡

በጤና ልማትሥራዎች ዘርፍ

➣ የወባ በሽታ መከላከልና መቆጣጠርን በተመለከተ በክልሉ ውስጥ ከፍተኛ የወባ ጫና ባለባቸው 50 ወረዳዎች 1,236,286 የአልጋ አጎበር እንዲሰራጭ ተደርጓል፡፡

➣ ከፍተኛ የወባ ጫና ባለባቸው በተለዩ 8 ወረዳዎች 31,835 ርጭት ኬሚካል የርጭት ሥራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

➣ በ54 ወረዳዎችና ከተማ አሰተዳደሮች 1,250,352 ሚሊ ሊትር የወባ ትንኝ ዕጪ መግደያ ኬሚካል ጥቅም ላይ ውሏል፡፡

➣ ሌሎች ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በክልሉ የጤና ተቋማት አክሞ ከማዳን ረገድ የተሻል አፈፃፀም ተመዝግቧል፡፡

➣ ከእናቶች ህፃናት ጤና አገልግሎት ማቅረብ የተቻለ ሲሆን በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን በቁጥር 48 የከተማና ገጠር ወረዳዎች የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን በማስፋት 300 ሺህ በላይ አባላት በማፍራት መቻሉን፡፡

➣ በማህበረሰብ ጤና መድን ከ118 ሚሊዮን 831 ሽህ 300 ብር በመሰብሰብ ባንክ እንዲገባ ተደርጓል፡፡

➣ ከጤና ሚኒስቴርና አጋር ድርጅቶች ከ83 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት መድሃኒት፤ የህክምና መገልገያዎች መሣያዎችን በድጋፍ በማግኘት ለጤና ተቋማት ማሰራጨት ተችሏል፡፡

➣ ከጤና ሚኒስቴርና አጋር ድርጅቶች ከ83 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት መድሃኒት፤ የህክምና መገልገያዎች መሣያዎችን በድጋፍ በማግኘት ለጤና ተቋማት ማሰራጨት ተችሏል፡፡

➣ ከልማት አጋሮች ጋር በመቀናጀት በክልሉ ለተለያዩ የጤና ተቋማት ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ ሀብት የግባዓት ማሟላትና የህኪም መገልገያ ቃሳቁስ ማቅረብ መቻሉን፡፡

➣ የማሻ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግንባታ ለማጠናቀቅ የክልሉ መስተዳድር ም/ቤት ተጨማሪ 10 ሚሊዮን በላይ ብር በመመደብ ግንባታዉ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡

➣ በካፋ ዞን ቆንዳ እና ዳዉሮ ዋካ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች ግንባታ ስራዎች በጥሩ እንቅስቃሴ ላይ በመሆናቸዉ የአንደኛ ዙር ክፍያ ወሰደዉ ስራ ላይ ይገኛሉ፡፡

➣ የቀሺ ጤና ጣቢያ እና ዳካ ጤና ጣቢያ የባለሞያዎች መኖሪያ ግንባታ እንዲሁም ምዕራብ ኦሞ ኦልኩት እና ሸካ ዞን ቄጃ ጤና ጣቢያዎች አንደኛ ዙሪ ክፍያ እየተፈፀመ ይገኛል፡፡

➣ በም/ኦሞ ዞን በጋችት ወረዳ የሚገነባው አዲሱ ጤና ጣቢያ የጨረታ ሂደቱ አልቆ ለተቋራጩ የቦታ ርክክብ በማደረግ የቅድመ ክፍያ ለመክፈል በዝግጅት ይገኛል፡፡

➣ በኮንታ ዞን የጨበራ ሻሾ ጤና ጣቢያ እና ደልባገነት ሁለተኛ ትዉልድ ጤና ኬላ ግንባታ ሙሉ ቅድመ ክፍያ ተፈጽሞ ወደ ስራ ገብተዉ የግንባታ ሂደቱ ጥሩ ደረጃ ላይ በመሆኑ ሁለተኛ ዙር ክፍያ ፈፅመን የተሻለ ስራ በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡

➣ የታርጫ ደም ባንክ ከተቋራጩ ጋር በመነጋገር ወደ ስራ እንዲገባ ተገርጓል፡፡

➣ የሴቶች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ከማሳደግ አኳያ በበጀት ዓመቱ በርካታ ተግባራት መከናወናቸዉን፡

➣ ከ 600 ሺህ በላይ ወጣቶች በክረምትና በበጋ ወራት መደበኛ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሰማርተው ከ2.2 ሚሊዮን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል፡፡

➣ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ሥራዎች አፈፃፀም

➣ በቱሪዝም ሀብቶች ልየታና የመዳረሻዎች የኢንቨስትመንትና የትውውቅ በርካታ ተግባራት መከናወናቸዉ፡፡

➣ በባህልና ቋንቋ ልማት እንዲሁም በስፖርት ዘርፍ በበጀት ዓመቱ አመርቂ ዉጤት መመዝገቡን፡፡

ከሠላምና ጸጠበሚመለከት

➣ በክልሉ በሱሪ እና በዲዚ ማሀብረሰ መካከል ተቋርጦ የነበረው ማህበራዊ ግንኙነት እንደገና እንዲጀምር ሰፊ ውይይት በማድረግ እርቅ ማውረድ ተችሏል፡፡

➣ ከጋምቤላ ክልል ጋር የነበረውን ግንኙነት ወደ ጋራ ፎረም በማሳደግ በክልሉ አጎራባች አካባቢዎች የሚፈጠሩ ህገ ወጥ ድርግቶች በትብብር በመቆጣጠር ላይ መቻሉን፡፡

➣ የህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በተደረገው ጥረት 209 የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች፣179 መሰል ካርታዎች ፤ 3,396 የተለያዩ መሳሪያ ጥይቶችና 6 ቦምቭ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ለምክር ቤቱ አብራርተዋል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *