በበጀት ዓመቱ የፕሮጀክቶች አፈጻጸል መሻሻል ታይቶባቸዋል ፡፡

Spread the love

ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ሪፖርት ማቅረባቸዉን እንደቀጠሉ ነዉ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በማዕድን ዘረፍና በመስኖ ልማት አውታሮች ዙሪያ የተሻሉ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ለምክርቤቱ ባቀረቡት የአፈጻጸም ሪፖርት አመላክተዋል ፡፡

ለመስኖ የተጠና የመሬት ሽፋን ከ22,120 ሄ/ር ወደ 29,430 ሄ/ር ለማሳደግ ታቅዶ የአራቱ ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል ፡፡

የ8 መስኖ ፕሮጀክቶች የግንባታ ሥራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለቀጣይ በጋ መስኖ ዝግጁ ማድረግ ተችሏል፡፡

የውጭ ምንዛሪ ግኝትን ለማሳደግ በባህላዊ ወርቅ ምርትና ግብይት ዙሪያ በተካሄደው እንቅስቃሴ 90 ኪ.ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ቀርቧል ፡፡

በዚህም በክልሉ መንግስት እየተገነቡ ያሉ 3 መናኸሪያዎች ግንባታ ፊዚካል አፈጻጸማቸው የቦንጋ መናኸሪያ 50%፣ የሚዛን መናኸሪያ 70% እንዲሁም የታርጫ መናኸሪያ 80% ደርሰዋል ፡፡

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 289,915,744 ብር ለመንገድና ድልድይ ግንባታ እና ጥገና ከሕብረተሰቡ እና ከባለድርሻ አካላት ሀብት መሰብሰብ ተችሏል፡፡

231 ኪ.ሜ የሚሸፍን 17 የመንገድ ፕሮጀክቶች ተጠናቀዋል።

የድልድይ ግንባታ ሥራን በተመለከተም በሚዛን ዲስትሪክት፣ የአጉ ድልድይ ግንባታ ቤንች ሸኮ ዞን በሰሜን ቤንች እና በሸኮ አካባቢ የሚገኝ ሲሆን ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል፡፡

የዳማ ወንዝ ድልድይ ግንባታ ሥራዎች ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል፡፡

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *