ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ለምክርቤት ካቀረቧቸው ሪፖርቶች

Spread the love

በበጀት ዓመቱ ብር 5,961,347,451.6 (95.5%) ገቢ ተሰብስቧል፡፡

በሁሉም መዋቅሮች በተደረገው ልዩ ድጋፍና ክትትል በበጀት ዓመቱ ለ64 ሺ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል፡፡

16 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 141 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ወደ ሥራ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡

የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ በክልላችን በምዕራብ ኦሞ ዞን በመኤኒት ሻሻና ማጂ ወረዳ እና በካፋ ዞን ጎባ ወረዳ በድምሩ 38,216 ሄክታር መሬት ልኬት በማድረግ የአካባቢው አስተዳደር ከኢንቨስትመንት መሬት ልማት ማግኘት የሚገባውን ታክስና ግብር እንዲያገኝ እየተደረገ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡

በምዕራብ ኦሞ ዞን ለረጅም ጊዜያት ሳይለማ የቆየውን የእርሻ መሬት ወደ ልማት ከማስገባት አንጻር ክልሉ፣ የፌዴራል መንግሥት እንዲሁም የውጭ ሀገር ባለሃብቶችን ያሳተፈ ጥምር የኢንቨስትመንት ዕቅድ ተዘጋጅቶ በሳይ እና ኮካ አካባቢ ሰፋፊ የእርሻ ኢንቨስትመንት ሥራ ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አብራርተዋል ፡፡

ይህም ለአካባቢው ሰፊ የሥራ ዕድል የሚፈጥርና በቀጠናው ሠላምና ልማት ለማረጋገጥ ዓይነተኛ ሚና የሚጫወት እንደሚሆን ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፖርታቸዉ አብራርተዋል ፡፡

በታጠቅ አበበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *