በከተማው እየተከናወነ ያለው የተቀናጀ የኮርደር ልማት ስራው ከግብ እንዲደርስ የባለድርሻ አካላት ትብብርና ድጋፍ እንዲጠናከር ተጠየቀ።

Spread the love

የከተሜ ነዋሪዎችን የአኗኗር ዘይቤ ለማሻሻልና ከተሞችን የሚመጥን የመሰረተ ልማት አቅርቦት ለመዘርጋት በኢትዮጵያ በተለያዩ ከተሞች ተግባራዊ የኾነው የኮሪደር ልማት ስራ የከተሞችን ሥነ-ውበት በማሳደግ፣ አረንጓዴነትን በማስፋት መሰረተ ልማትን በማቀናጀት ባሻገር ተጨማሪ ጊዜያዊ የስራ ዕድሎችንም እየፈጠር ይገኛል።

በ31 የኢትዮጵያ ከተሞች ተግባራዊ የተደረገው የከተሞች የኮሪደር ልማት ስራ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በይፋ ከተጀመረበት የክልሉ ከተሞች ሚዛን አማን ከተማ አንዷ ሲትሆን ፕሮጀክቱ ስጠናቀቅ አጠቃላይ የከተማውን ደረጃ በማሻሻል ለነዋሪዎች ፍላጎቶች የተመቸ ያደርጋል ተብሎ ትልቅ ተስፋ ተጥሎበታል።

የተቀናጀ የኮሪደር የልማት ፕሮጀክቱ በከተማው ከዚህ በፊት ይስተዋል የነበረውን የልማት ክፍተት በመሙላት ተመራጭ የቱሪዝም እና የኢንቨስትመንት መዳረሻ እንዲሆኑ ከማስቻል ባለፈ በተቀናጀ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ በማስተሳሰር ቀልጣፋና ተደራሽ የመንግሥት አግልግሎት ለህዝብ ለማቅረብ የሚያስችል መሆኑን ነው የከተማው ከንቲባ አቶ ግሩም ተማም የገለጹት።

በከተማው እየተከናወነ ያለው የተቀናጀ የኮርደር ልማት ስራው ከግብ እንዲደርስ የባለድርሻ አካላት ትብብርና ድጋፍ እንዲጠናከር የጠየቁት ከንቲባው ፕሮጀክቱ ስጠናቀቅ የከተማውን ሁለንተናዊ ገጽታ በማሻሻል ሚዛን አማን ከተማን ወደ ላቀ ምቹ፣ ንቁ እና ተመራጭ የመኖሪያ ከባቢ የመለወጥ የመንግስት ጥረት አካል በመሆኑ በልዩ ትኩረት እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱ የከተማውና የሥራ ባህል የቀየር እንደሆነና በከተማው ለብዙ ስራ ፈላጊ ወጣቶች የሥራ ዕድል የፈጠረ መሆኑን ያነሱት አቶ ግሩም ከተማ አስተዳደሩ ከኮርደር ልማቱን ጎን ለጎን ወደ መልሶ ማልማት የገባ በመሆኑ ፕሮጀክቱ በከተማው የተለያዩ ልማቶችን ለማስተሳሰር እንደሚረዳም ተናግረዋል።

በፕሮጀክቱ አፈጻጸም ላይ ማብራሪያ የሰጡት የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ አሰፋ ቤሪ የኮርደር ልማት ስራውን ለማስጀመር የልየታና በቂ ቅደመ ዝግጅት በማድረግ ወደ ተግባር መገባቱን በመግለጽ በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ ቀን ከሌት በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።

የከተማው ነዋሪዎች ፕሮጀክቱን በመደገፍ እያሳዩት ያለው ተግባር አበረታች መሆኑን የጠቆሙት አቶ አሰፋ የህዝቡ ተሳትፎ እስከ ፕሮጀክቱ መጠናቀቅ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ከከተማው ነዋሪዎች መካከል ወ/ሮ ትዕግስት ለማ እና አቶ ብርሀኑ መኩሪያ እንደገለጹት ለልማት ስራው ስኬት ይዞታ በመላቀቅ እንዲሁም በስራው ላይ ለሚገኙት ባለሙያዎች የሞራል ድጋፍ በመስጠት የበኩላቸውን እየተወጡ እንደሆነ ተናግረዋል።

የሥራ ዕድል ከተፈጠረላቸው የከተማው ወጣቶች መካከል ወጣት ጌታቸው ባሽቃሪ እና ወጣት ወንድዬ ክዳኔ የኮርደር ልማት ልማቱ የሥራ ዕድል እንደፈጠረላቸው በመግለጽ በሚያገኙት ገቢ ቤተሰቦቻቸውን እያስተዳደሩ መሆኑን ተናግረዋል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *