ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ ካነሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል፡-

Spread the love

👉 የዋጋ ግሽበት ባለፉት ዓመታት በርካታ ሀገራትን ፈትኗል ፤ ኢትዮጵያም የዋጋ ግሽበትን ለመቅረፍ በርካታ ስራዎችን እያከናወነች ነው፤ በተለይም ምርት ማምረት ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

👉 በሀገሪቱ የሚስተዋለውን የዋጋ ግሽበት ለመቅረፍም ከ300 እስከ 400 ቢሊየን ዶላር ለድጎማ ተይዟል፡፡

👉 ባለፉት 3 ወራት ለነዳጅ ዘርፍ 35 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ተደጉሟል፤ በበጀት ዓመቱ ለሴፍቲነት 80 ቢሊየን ብር፣ ለዘይት 9 ቢሊየን ብር፣ ለማዳበሪያ 53 ቢሊየን ብር ለድጎማ ተመድቧል፡፡

👉 የደመወዝ ጭማሪውን በተመለከተ ከፍተኛ የዳታ ችግር ተፈጥሯል፤ ይህን ዳታ ለማጥራት ከፍተኛ ሥራ ሲሰራ ቆይቷል፡፡

👉 ለደመወዝ ጭማሪ 91 ቢሊየን ብር ተመድቧል፤ ጭማሪውም በተያዘው ጥቅምትር ወር ጀምሮ ተግባረዊ ይደረጋል፡፡

👉 በተያዘው በጀት ዓመት የዋጋ ግሽበት 17 በመቶ ሆኗል፤ ይህም ካለፉት ዓመታት አንጻር የተሻለ ሥራ መሰራቱን ያመላክታል፡፡

👉 ኢንዱስት ፓርኮች 50 በመቶ በሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ተይዘዋል፡፡

👉 ከነበሩበት 59 በመቶ የማምረት ዐቅም በዚህ ዓመት 67 በመቶ የምርት ዕድገት ይጠበቅባቸዋል ኢንዱስትሪ ፓርኮች፡፡

👉 124 አዳዲስ አውሮፕላኖች አዝዘናል፡፡ በኢትዮጵያ ሁለተኛ የሆነውን አውሮፕላን በእጥፍ ለመብለጥ እየተሠራ ነው፡፡

👉 በአፍሪካ ትልቁን የአውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት እየሠራን ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *