


የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሥነ-ምግባር እና ፀረ- ሙስና ኮሚሽን ከባለድርሻ አካላት ጋር በቦንጋ ከተማ መከረ።
ኮሚሽኑ በ2015 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸምና የ2016 ጠቋሚ ዕቅድ ዙሪያ ከዞንና ከክልል ተቋማት ከተወጣጡ የሥነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ባለሙያዎችና አመራሮች ጋር የአንድ ውይይት አካሂዷል።
የፀረሙስና ትግሉን ህዝባዊ መሠረት በማስያዝ የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ የገለጹት የክልሉ የሥነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሉሰው ዘውዴ የተጀማመሩ የፀረ-ሙስና ትግሎች ውጤት እያመጣ መሆኑን ተናግረዋል።
እንደ ኮሚሽነሩ ገለጻ በተጠናቀቀው የ2015 በጀት ዓመት በአስቸኳይ ሙስና መከላከልና በኦዲት ግኝት የተመዘበረ ከ36 ሚሊዮን ብር በላይ የመንግስት ሀብት ማስመለስ መቻሉን ተገልጿል።
የጥቅም ግጭትና ሙስናን ለመከላከል በተሰራው ስራ በክልሉ የ8 መቶ 97 በተለያየ ደረጃ የሚገኙ አመራሮች የሀብት ምዝገባ ማከናወን መቻሉ የጠቆሙት ኮሚሽነሩ የሀብት ምዝገባና ማጣራት ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግሯል።
በክልሉ በተጠናቀቀው የ2015 በጀት ዓመት የመንግስት አሰራርን በማይመች አኳን የመሩ 49 ግለሰቦች በ69 የክስ መዝገቦች በፍርድ ቤት ቀርበ ተጠያቂ መሆናቸውን ከቀረበው ሪፖርት መገንዘብ ተችሏል።
በ2016 የበጀት በኮሚሽኑ በተለዩ አምስት የትኩረ መስኮች ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥል የተገለጸ ሲሆን የተቋማት አመራርና ሠራተኞች የስነምግባር ግንባታና የሙስና መከላከል አቅም ማሳደግ ላይ ትኩረት እንዲሰጡ ተጠይቋል።
መንግሥት ለፀረ ሙስና ትግል የሰጠውን ትኩረት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀምና ከሌሎች ተቋማት ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር ለፀረ ሙስና ትግል በአጽንኦት መስራት አለብን ሲሉ የመድረኩ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።
በየአከባቢው ለልማት የሚመደበው በጀት ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ልዩ ትኩረት መሰጠት እንዳለበት የጠየቁት የመድረኩ ተሳታፊዎች በየደረጃው ባለው መዋቅር የሰው ሀብት ጉድለት ያለ በመሆኑ የማሟላት ስራ ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቀዋል።
በመድረኩ የ2015 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2016 ጠቋሚ ዕቅድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።



በዕድገቱ በዛብህ
