


ኢትዮጵያ ያዘጋጀችው ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት ኮንፈረንስ ዛሬ በአዲስ አበባ ተከፍቷል።
ይህንን ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት ኮንፈረንስ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ፣ የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዱዓለም እና የመሀመድ ቢን ዛይድ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ዶክተር ከሊፋ ሙባረክ ከፍተውታል።
በኮንፈረንሱ ላይ ከ16 ሀገራት የተውጣጡ የሃይማኖት አባቶችና የተቋማት መሪዎች እየተሳተፉ ነው።
ኮንፈረንሱ በልዩ ልዩ መርሀ ግብሮች እስከ ነገ እንድሚቀጥል ታውቋል ሲል ኢፕድ ዘግቧል።
