










ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ረሃብን መዋጋት የጋራ ምላሽን ይሻል ሲሉ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤የ”ከረሃብ ነፃ ዓለም” ጉባኤን ስናጠናቅቅ እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ውይይቶች የተሳኩ ይሆኑ ዘንድ አስተዋፅዖ ያበረከቱትን ተሳታፊዎች ከልብ አመሰግናለሁ ብለዋል፡፡
በመልዕክታቸው ረሃብን መዋጋት የጋራ ምላሽን ይሻል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለዚህም ለምግብ ዋስትና የሚሆን የዓለም አቀፍ ድጋፍ አቅርቦት፣ድንበር ዘለል የሆነ የእውቀት ማካፈል ልምምድ፣ ለፍትሃዊ ተደራሽነት የሚረዳ የፖሊሲ መናበብ ብሎም ለሴቶች ትኩረት የሚሰጥ የአነስተኛ አርሶና አርብቶ አደሮች ድጋፍ ሥራ አስፈላጊ መሆኑንም ገልጸዋል።
አርባ ቢሊዮን ዛፎች በተተከሉበት ምርታማነትን በሚያሳድጉ የለውጥ ሥራዎች፣ ድርቅን በሚቋቋሙ አዝርዕት ልማት፣ በአረንጓዴዓሻራ መርሃ ግብር ሥራዎች አማካኝነት በዘላቂ የግብርና ሥራ የታየው የኢትዮጵያ ርምጃ በጉባኤው ቀርቧል ሲሉም አስታውቀዋል።
በ’ኢትዮዽያ ታምርት’፣ በአግሮ ኢንደስትሪ ፓርኮች ጥምር የሥራ ፈጠራ ሥራ፣ በገቢ እድገት እና ጽናት የታዩት ኢንቨስትመንቶች በአለም የግብርና ዘርፍ የኢትዮጵያን ሚና አጠናክረውታል ነው ያሉት ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።
