የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና ቢግ ዊን ፊላንትሮፒ በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ዛሬ ተፈራርመዋል

Spread the love

የመግባቢያ ሰምምነቱን የተፈራረሙት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል እና የቢግ ዊን ፊላንትሮፒ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ከሰተብርሃን አድማሱ ናቸው።

የመግባቢያ ስምምነቱ ለሚኒስቴሩ ራዕይ ስኬታማነት ለፕሮጀክቶች ቴክኒካል ድጋፍና ክትትል ለማድረግ እንዲሁም የአፈጻጸም አቅምን ማጎልበት ዓላማ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

በጨርቃ ጨርቅ፣ በእርሻ ውጤቶች፣በቆዳ፣ በኬሚካል እና ኮንስትራክሽን፣ በቴክኖሎጂ፣ በፋርማሲ ውጤቶች የስራ ዕድል መፍጠር የስምምነቱ አንድ አካል ነው።

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እ.አ.አ በ2030 ኢትዮጵያን የአፍሪካ የኢንዱስትሪ ማዕከል እንድትሆን የማስቻል ራዕይ አንግቦ እየሰራ እንደሚገኝ ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *