የምስራቅ አፍሪካ ዓመታዊ የፋይናንስ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሔድ ጀመረ::

Spread the love

ለሰባተኛ ጊዜ በሚካሄደው የፋይናንስ ጉባኤ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱን ጨምሮ፣ የባንክ ሀላፊዎች፣ የኢንሹራንስ ተቋማት ተወካዮችና የፋይናንስ ዘርፍ ተዋናዮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ መቋቋም የሚችል ምጣኔ ሀብትን መገንባት፣ በምስራቅ አፍሪካ ትስስርን መፍጠር ፣ ኢኮኖሚያዊ እድሎችን ጨምሮ የፋይናንስ ዘርፉን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ማድረግ በጉባኤው ለውይይት ከተያዙ አጀንዳዎች ውስጥ ናቸው።

በተመሳሳይ ኢትዮጵያ የካፒታል ገበያን በማቋቋም ምህዳሩን ምቹ ለማድረግ እያከናወነች ያለው ተግባርና ይዞት የሚመጣው እድል በጉባኤ ይቀርባል።

የምስራቅ አፍሪካ ዓመታዊ የፋይናንስ ጉባኤ በምስራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ዘርፍ ትስስርን ለማጠናከር፣ ልምድና ተሞክሮ ለመለዋወጥ እንደሚረዳ ተጠቁሟል።

ዓለም አቀፍና ቀጣናዊ ስጋቶችን በጋራ መፍትሔ ለማበጀት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደሚደረግ ተገልጿል።

የፋይናንስ ጉባኤው፤ የፖሊሲ ምክረ ሀሳቦችን ለመጠቆም፣ የገበያ ዕድሎችን ለመጠቀም፣ በቀጣናው እንዲሁም በአህጉሩ የፍይናንስ ዘርፍን ምህዳርን ምቹ ማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ የመምከር አላማ አንግቦ የተቋቋመ ነው።

ጉባኤው ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት ነው የሚካሔደው ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *