ግብርናውን በቴክኖሎጂ፣ በፋይናንስና በክህሎት የታገዘ እንዲሆን በማድረግ በዚህ አመት 6.8 በመቶ ዕድገት ለማስመዝገብ ይሰራል፦ ፕሬዚዳንት ታዬ
የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ 6ኛው የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮችና ፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን የጋራ መክፈቻ ላይ ባለፈው አመት ከግብርናው ዘርፍ 1 ነጥብ 57 ቢሊዮን ኩንታል ምርት መገኘቱን አንስተዋል፡፡ በ2018 ዓ.ም የተፈጥሮና ውጫዊ ተጽዕኖን የሚቋቋም ኢኮኖሚ በመገንባት ሂደት ግብርናው ትልቅ ድርሻ እንደሚኖረው ፕሬዚዳንቱ አንስተዋል፡፡
ግብርናው በቴክኖሎጂ፣ በፋይናንስና በክህሎት የታገዘ እንዲሆን በማድረግ 6.8 በመቶ ዕድገት ለማስመዝገብ እንደሚሰራና በሌማት ትሩፋት፣ በከተማ ግብርና፣ በስንዴ ልማትና በሌሎች የተገኙ ተሞክሮዎችን በማስፋፋት በዜጎች ላይ የሚደርሱ የኑሮ ጭናዎችን ለመቀነስ ትኩረት ይደረጋል፡፡
ማደበሪያ እና ሌሎች የግብርና ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት የሚደረግ ሲሆን የማዳበሪያ ፋብሪካው የመሰረት ድንጋይ መጣሉ ለዚህ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
