የዲፕሎማሲያችን ማጠንጠኛው ብሔራዊ ጥቅም እና የዜጎች ክብር ነው፦ ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀ ሥላሴ

Spread the love

የዲፕሎማሲያችን ማጠንጠኛው ብሔራዊ ጥቅም እና የዜጎች ክብር ነው፦ ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀ ሥላሴ

ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀ ሥላሴ በሁለቱ ምክር ቤቶች የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የዲፕሎማሲያችን መሰረታዊ ማዕከል እና ማጠንጠኛው ብሔራዊ ጥቅም እና የዜጎች ክብር ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ጂኦስትራቴጂያዊ ቁመና በመደርጀት ላይ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ይህ ስትራቴጂያዊ ምርጫ ከታዛቢነት ወደ አጀንዳ ተላሚነት እና ተጽዕኖ ፈጣሪነት ለመሸጋገር አስችሎናል ነው ያሉት።

ኢትዮጵያ በድንበር ተሻጋሪ ሀብቶቿ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ስትቀበል፤ በዛው ልክ ደግሞ አስተማማኝ የባሕር በር ተጠቃሚነት መብቷን ማረጋገጥ እንዳለባት አንስተዋል።

በሀገሪቱ የህልውና ጉዳዮች በሆኑት ሁለቱ ታላላቅ የውኃ ሀብቶች ዙሪያ መንግሥት ያልተቋረጠ ሰላማዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን በማድረግ ላይ እንደሚገኝም ገልፀዋል።

እስካሁን በተደረጉ ጥረቶች ታላቁ የሕዳሴ ግድብ አጋጥመውት የነበሩትን ፈተናዎች በጥበብ በማለፍ ማጠናቀቅ እና ማስመረቅ መቻሉን አስታውሰዋል።

ከዚህ ባለፈም አስተማማኝ እና ዘላቂነት ያለው የባሕር በር የማግኘት ጉዳይ ከፍ ወዳለ ደረጃ መሸጋገሩን ያነሱትፕሬዚዳንቱ፤ በውጭ ሃገር ለእንግልት የተዳረጉ ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ማድረግ መቻሉን አንስተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *