
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፍላጎት የማሳኪያ ስልት (ልምምድ) ችግር አለበት፤ በዚህም ከውይይት ይልቅ ጠመንጃ ማንሳትን ያስቀደመ መሆኑ ትክክል አለመሆኑን አንስተዋል፡፡
በጦርነት የሚገኝ ጥቅም የለም፤ ጥቅም ያለው ከሠላም ነው፤ ይህን ሁልጊዜም መገንዘብና መኖር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ከሸኔ ጋር የተካሄደው ድርድር ለሕዝብ ይፋ የምናደርገው የተጨበጠ ጉዳይ ስለሌለ ነው ይፋ ያልተደረገው፤ በቀጣይ ተጨባጭ ጉዳይ ሲኖር ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይፋ ይደረጋል፡፡
ከሽምቅ ተዋጊ ጋር ድርድር ማድረግ በኢትዮጵያ አልተጀመረም፤ በዓለም ላይ በተለያዩ ሀገራት የሚተገበር ነው ብለዋል፡፡
የራስን ሕዝብ እየበደሉ እታገልልሃለሁ ማለት ተገቢ አይደለም፤ ልቦና ገዝቶ ወደ ውይይትና ሠላም መምጣት እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ በምርጫ እና በዴሞክራሲ ካልሆነ በአፈሙዝ ስልጣን ይዞ ማሥተዳደር እንደማይቻልም በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡
