የምክር ቤቱ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እስካሁን ያቀረቧቸው ዋና ዋና ጥያቄዎች

Spread the love

👉 ከአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ጋር የተደረገው ንግግር ያልተሳካው በምን ምክንያት ነው፤

👉 በአማራ ክልል የተወሰደው ህግ የማስከበር እርምጃ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል፤

👉የአማራ ክልል ነባራዊ ሁኔታ ከውጭ ሃይሎች ጣልቃ ገብነት ምን ያህል የጸዳ ነው፤

👉 መንግስት የተዛቡ ችግሮችን ለማረምና አሰባሳቢ ትርክት ለመገንባት እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን የተመለከተ ማብራሪያ ቢሰጥ፤

👉 በመንግስትና በፓርቲ ውስጥ ያሉ ዋልታ ረገጥ አስተሳሰቦች ያላቸው ተዋንያንን ለማስተካከል ምን ያህል ዝግጁ ነው ምንስ እየተሰራ ነው፤

👉 መንግስት የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት ፍላጎት አለው፤ ይሄንንም በህግና በአሰራር እየተገበረ ነው፤ ይሁንና ከመንግስት ጋር ልዩነት ያላቸው ሰዎች ላይ ወከባ እያደረሰ እንደሆነ ይገለጻል፤ መንግስት አምባገነን እየሆነ ነው ለሚለው ምን ምላሽ አለዎት፤

👉 የዋጋ ንረት መባባስ፣ የንግድ ስርዓቱ ችግር ያለበት መሆኑ ይታወቃል፤ ከማክሮ ኢኮኖሚ አመላካች ነጥቦች አንጻር ኢኮኖሚው ያለበት ደረጃ ቢገለጽ፤

ኢትዮጵያ በውጭ ብድር የዩሮ ቦንድ ወለድን መክፈል አልቻለችም የሚል መረጃ ተሰራጭቷልና በዚህ ጉዳይ ማብራሪያ ቢሰጡን፤

👉የማዳበሪያ ስርጭትና ምዝበራን ለመከላከል ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ይታወቃል፤ ነገር ግን በአንድ አንድ ክልሎች አሁንም ጥያቄ እየተነሳ ነውና ምን እየተሰራ ነው፤

👉 የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል አዲስ በመሆኑ የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ የታሰበ ነገር ካለ ቢብራራ፤

👉 ከሶማሌላንድ ጋር የተፈጸመው ስምምነት በዓለም ላይ በተፈጠሩ ውጥረቶች ምክንያት አካባቢው ችግር ውስጥ ባለበት ወቅት፤ አልሸባብ ባልተገታበት፤ ግብጽ አሁንም ኢትዮጵያን ለመጉዳት እያሴረች ባለችበት ወቅት መሆኑ ውሳኔው በጥበብ ይመራል ብዬ አምናለሁ።

👉 ይህንን ስምምነት ተከትሎ የተነሳውነ ጩህት ለመመከት በመንግስት በኩል ምን ዝግጅት ተደርጓል፤

👉 በሶማሌ ላንድና በኢትዮጵያ መካከል የተፈጸመው ስምምነት በአፍሪከ ህብረት እና በተመድ በኩል የአገሪቷ ጉዳይ እልባት ያልተሰጠው በመሆኑ አጣብቂኝ ውስጥ ሊከተን ይችላልና፤ ምን ያህል ጥልቀት ያለው ዲፕሎማሲ እየተሰራ ነው፤

👉 የገጠሩ ህዝብ የስልክ ኔትወርክ ተረስቻለሁ እያለ ነውና የታሰበ ነገር ካለ ቢብራራ፤

👉 የተጀመሩና ግንባታቸው ያልተጠናቀቁ ግዙፍ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ምን ታስቧል፤

👉 የድርቅ አደጋን ለመመከት መንግስት እየሰራ ያለው ስራ አነስተኛ እንደሆነ ይነገራል፤ መንግስት እየሰራ ያለውን ስራ በተመለከተ ማብራሪያ ቢሰጥ፤

👉 የስፖርት ጨዋታዎች ውርርድ አዲስ ልምድ እየሆነ መጥቷል፤ ይህ ነገር ለህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርና ለወንጀል ብሎም ለሱስና ለሌሎች ማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮች የሚዳርግ ነው፤ ሌሎች አገራት ይሄንን ተረድተው ከልክለዋል፤ በአገራችን ነባራዊ ሁኔታ በብዛት እየተስፋፋና ጉዳት አያደረሰ ነውና ይህንን መንግስት እንዴት ይመለከተዋልል፤ ምን ልዩ ትኩረትስ ተሰጥቷል፤

👉 ከዲያስፖራው ማህበረሰብ ጋር ያለውን ፖለቲካዊ ቅራኔዎችን ለመፍታት የታሰበ ነገር ካለ ቢብራራ፤

👉 እንደ አልሸባብ ያሉ አሸባሪዎችን በቀጣናችን ለመከላከል አገራችን ያላት የመሪነት ደረጃ ምን ይመስላል፤

👉ከሶማሌ ላንድ ጋር የተደረገውን ስምምነት በተመለከተ ተጨማሪ ማብራረሪያ ቢሰጡበት፤ ይሄንን ተከትሎ የሚመጡ ጫናዎችን ለመመከትና የሚቃጣ የሀይል እርምጃም ካለ ለመከላከል መንግስት እያደረገ ያለው ዝግጅት ምን ይመስላል፤

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *