ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአማራ ክልል ሁሉም ዞኖች በተደረገው ውይይት ከህዝቡ ሶስት ዋና ዋና ጥያቄዎች መስተዋላቸውን አንስተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ክልሉን በተመለከተ ምላሽ ሲሰጡ የልማት፣ የህገ መንግስት ማሻሻልና የወሰን ጥያቄዎች በተደረገው ውይይት ከህዝቡ የተነሱ ዋና ዋና አጀንዳዎች ናቸው ብለዋል፡፡
መንግስት በአማራ ክልል የሚነሱ የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ ብዙ ርቀት ሄዷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለአብነትም 2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር አውጥተን በአባይ ወንዝ ላይ በአይነቱ ልዩ የሆነ ድልድይ መገንባቱን ገልጸዋል።
በጎርጎራ ፕሮጀክት አማካኝነትም የክልሉን ቱሪዝም የሚያነቃቃ ስራ እንደተከናወነም አንስተዋል፡፡
በአገራዊ የምክክር ኮሚሽን በኩል ሌሎች ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ የሚሰራ ይሆናል ሲሉም ተናግረዋል።
በአማራ ክልል የሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ ቁርጠኛ አቋም ይዘን በ5 ዓመታት 3 ሺሕ 200 ኪ.ሜ የመንገድ ዝርጋታ ጀምናል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
ከዚህ ውስጥ 130 ኪ.ሜ ተጠናቋል፤ በባህር ዳር 2 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር አውጥተን ድልድይ ሰርተናል ነው ያሉት።
